በደመና ይመለሳል
Bedemena Yemelesal
2010 · ትራክ 8 · 4:00 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በደመና ይመለሳል
በሚያስደንቅ ክብር ይገለጣል
ልጆቹን ፍለጋ ይመጣል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አባት እንደሌለው አልተዋችሁም
ስፍራን ላዘጋጅ እንጂ እንድወስዳቹህ
ልባቹን አይፍራ በእኔ እመኑ
ቶሎ እመልሳለሁ ልወስዳቹህ
አዝማች · Chorus
በደመና ይመለሳል
በሚያስደንቅ ክብር ይገለጣል
ልጆቹን ፍለጋ ይመጣል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንኳን መኖሪያችን ቤታችን
ሊፈርስ ተስፋ ቢያጣ ኑሯችን
በእጅ ያልተሰራ ጌታ ያዘጋጃል
ተስፋችን ላይኛይቱ ጽዮን ናት
አዝማች · Chorus
በደመና ይመለሳል
በሚያስደንቅ ክብር ይገለጣል
ልጆቹን ፍለጋ ይመጣል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በዚህ ዓለም ኑሯችን ያበቃል
ጌታ ኢየሱስ ሊወስደን ይመጣል
ብርሃን በሞላባት ቅድስት ሃገር
ጊዜው ደርሷል እንሂድ እንዘምር
አዝማች · Chorus
በደመና ይመለሳል
በሚያስደንቅ ክብር ይገለጣል
ልጆቹን ፍለጋ ይመጣል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ