Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መላእክት አዲስ ቅኔ

Melaekt Adis Qenie

2010 · ትራክ 5 · 3:49 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው

በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት

በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሃፍ አየሁ

ብርቱም መልአክ "መጽሃፉን ይዘረጋ ዘንድ ፤

ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማነው?"

ብሎ በታላቅ ድምጽ ሲያውጅ አየሁ

በሰማይም ቢሆን ፤ በምድርም ቢሆን ፤

ከምድርም በታች ቢሆን ፤ መጽሃፉን ሊዘረጋ ወይም

ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም መጽሃፉንም ሊዘረጋ

ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልነበረ

እጅግ አለቀስኩ ከሽማግሌዎቹም አንዱ

"አታልቅስ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ

እርሱም የዳዊት ስር መጽሃፉን ይዘረጋ ዘንድ

ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነስቷል" አለኝ [1]

መልአክት አዲስ ቅኔ ይዘምራሉ

እንዲህ እያሉ መጽሃፍት ወስደን

ማኅተሞቹን ትፈታ ዘንድ ይገባሃል

ይገባሃል (፫x) ታርደሃልና ትፈታ ዘንድ ይገባሃል

ሌሎች ሲሉ ሰማሁ የታረደው በግ

ሃይልና ባለጠግነት ፣ ጥበብ ብርታት ፣ ክብር ምሥጋና በረከት

ይቀበል ዘንድ ይገባዋል (፪x) በረከትን ይቀበል ዘንድ ይገባዋል

በረከት እና ክብር ምሥጋና ሃይልም

ከዘለዓለም እስከዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው በጉ ይሁን

ደግሞ እያሉት ቅዱሳኑ ለበጉ ክብር

ይቀኛሉ ይዘምራሉ ያዜማሉ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ