Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ

YeEgziabhier Kend Hoy

2010 · ትራክ 9 · 5:51 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ (፫x) በእኛ

ከጥንት የነበረው ያ ታላቅ ግሩም ሃይል

ዛሬም ይንቀሳቀስ በእኛ (፪x)

ለእስራኤላውያን የእሳት ታንኩናቸው

በደመና ጋርደስ ከክፉ አዳንካቸው

እናምናለን በሃይልህ በቃልህ

እግዚአብሔር ሆይ ተነስ ሃይልህ ይፍሰስ

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ (፫x) በእኛ

ከጥንት የነበረው ያ ታላቅ ግሩም ሃይል

ዛሬም ይንቀሳቀስ በእኛ (፪x)

በምድረበዳ ቢራቡ መናን መግበህ ጠገቡ

ደግሞም እንዳይጠማቸው አስበህ

ከአለት ውሃን አፈለቅህ

ልብሳቸው ነበር ጌታቸው ጉልበት መጠጊያ ሃይላቸው

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ (፫x) በእኛ

ከጥንት የነበረው ያ ታላቅ ግሩም ሃይል

ዛሬም ይንቀሳቀስ በእኛ (፪x)

በሙሴ ውስጥ ሆነህ የሰራህ

የኤልያስ አምላክ ወዴት ነህ

አልረሳንም ከቶ ተስፋህን

እንደምሰጠን ሃይልህን

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ (፫x) በእኛ

ከጥንት የነበረው ያ ታላቅ ግሩም ሃይል

ዛሬም ይንቀሳቀስ በእኛ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ