Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምሥጋና ይገባሃል

Mesgana Yegebahal

2010 · ትራክ 10 · 5:56 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምሥጋና ይገባሃል ጌታ ሆይ

ምህረትህ በእኛ ላይ ናትና

መንግሥትም የአንተ ናት ጌታ አምላክ ሆይ

ክብር ይገባሃል ክብር ሃሌሉያ

እግዚአብሔር በመንገዱ ጻድቅ ነው

ከቁጣም የራቀ ይቅር ባይ ነው

ጌታ እሩህሩህና መሃሪ ነው

ምሥጋና ይገባሃል ጌታ ሆይ

ምህረትህ በእኛ ላይ ናትና

መንግሥትም የአንተ ናት ጌታ አምላክ ሆይ

ክብር ይገባሃል ፤ ክብር ሃሌሉያ

ጌታ በቃሎቹ ታማኝ ነው

በስራውም ሁሉ ምስጉን ነው

ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው

ምሥጋና ይገባሃል ጌታ ሆይ

ምህረትህ በእኛ ላይ ናትና

መንግሥትም የአንተ ናት ጌታ አምላክ ሆይ

ክብር ይገባሃል ፤ ክብር ሃሌሉያ

የተፍገመገሙትን የሚደግፍ

የወደቁትን የሚያነሳ

ማነው እንደአንተ ያለ አጽናኝ ጌታ

ምሥጋና ይገባሃል ጌታ ሆይ

ምህረትህ በእኛ ላይ ናትና

መንግሥትም የአንተ ናት ጌታ አምላክ ሆይ

ክብር ይገባሃል ፤ ክብር ሃሌሉያ

የሁሉም ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል

እጅህን ትከፍታለህ ይጠግባሉ

ክቡር ስምህንም ያከብራሉ

ምሥጋና ይገባሃል ጌታ ሆይ

ምህረትህ በእኛ ላይ ናትና

መንግሥትም የአንተ ናት ጌታ አምላክ ሆይ

ክብር ይገባሃል ክብር ሃሌሉያ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ