በዓለም ከሚገኝ
Bealem Kemigegn
2010 · ትራክ 13 · 4:07 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዓለም ከሚገኝ ብዙ ክብር ይልቅ
ስለ ክርስቶስ መነቀፍን የሚበልጥ
ብድራቱን ትኩር ብሎ አይቷልና
ሙሴ ጌታን አከበረው በሕይወት ጐዳና
ቁጥር 1 · Verse 1
ለጊዜው በኀጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ
ለጌታ መነቀፍ እጅግ እንደሚበልጥ
ታውቆት ክብሩን ተወ በእግዚአብሔር ተማምኖ
ጌታም አልተወውም አየሁ ልጄ ብሎ
አዝማች · Chorus
በዓለም ከሚገኝ ብዙ ክብር ይልቅ
ስለ ክርስቶስ መነቀፍን የሚበልጥ
ብድራቱን ትኩር ብሎ አይቷልና
ሙሴ ጌታን አከበረው በሕይወት ጐዳና
ቁጥር 2 · Verse 2
የማይታየውን በእምነት እያየ
የዓለምን ክብር ሁሉ ስለ ጌታ ጣለ
ጌታም አከበረው ልጁን አልተወውም
ፀጋን አለበሰው ዓለም የማያየውን
አዝማች · Chorus
በዓለም ከሚገኝ ብዙ ክብር ይልቅ
ስለ ክርስቶስ መነቀፍን የሚበልጥ
ብድራቱን ትኩር ብሎ አይቷልና
ሙሴ ጌታን አከበረው በሕይወት ጐዳና
ቁጥር 3 · Verse 3
እምነቴን በስራ እንድገልጠው
የግለት መንፈስህን በሕይወቴ አብዛው
እስከሞትም እንኳ ለስምህ
ለመጋደል አብቃኝ እባክህ
አዝማች · Chorus
በዓለም ከሚገኝ ብዙ ክብር ይልቅ
ስለ ክርስቶስ መነቀፍን የሚበልጥ
ብድራቱን ትኩር ብሎ አይቷልና
ሙሴ ጌታን አከበረው በሕይወት ጐዳና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ