በኃይሌ እንዳልል
Behaylie Endalel
2012 · ትራክ 1 · 5:13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በኃይሌ እንዳልል ሰው አይበረታ በኃይሉ
አቅሜ እንዳልል የለኝም ጉልበት (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከእኔ ነው የምለው ምንም ነገር የለም
ለመዳኔ ምክኒያት ምንም አልፈጠርኩ
ታሪኬ እንዲያምር ከክብሩ ወረደ
ሕይወቱን ሊሰጠን እራሱን አዋረደ
ወዶኛልና አዳነኝ (፬x)
አዝማች · Chorus
በኃይሌ እንዳልል ሰው አይበረታ በኃይሉ
አቅሜ እንዳልል የለኝም ጉልበት
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰራሁት የምለው አከናወንኩት
ዛሬ ለመድረሴ እኔስ ለፋሁበት
የምለው የለኝ ድካሜ ነው ቀላ
ግን በእርሱ ምህረት እዚህ ደርሻለሁ
ወዶኛልና አዳነኝ (፬x)
አዝማች · Chorus
በኃይሌ እንዳልል ሰው አይበረታ በኃይሉ
አቅሜ እንዳልል የለኝም ጉልበት
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔን ለማዳን ነው ስቃዩ የበዛው
የደም ላብ ያላበው በመስቀል የሞተው
ሞቴን የሞተልኝ ነጻ አውጥቶኛል
የዘለዓለም መንግሥት ወራሽ አድርጐኛል
ወዶኛልና አዳነኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ