ላመስግንህ
Lamesgeneh
2012 · ትራክ 2 · 3:30 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ላመሰግንህ ይገባኛል
ዝምታ ከእኔ ሊርቅ ግድ ይለኛል
ውለታ ያለበት ሰው
መስዋዕቱ ሁሌ ምሥጋና ነው
አዝማች · Chorus
ላመስግንህ እጆቼን አንስቼ
ላመስግንህ በፊትህ ወድቄ
ላመስግንህ ጌታ ላመስግንህ
ላመስግንህ ኢየሱስ ላመስግንህን
ቁጥር 2 · Verse 2
ላመስግንህ ላመስግንህ
ተነሺ ዘምሪ ተቀኚ ለክብሩ
ይለኛል ሁልጊዜ የበዛ ምህረቱ
የሳቅ ሆኖልኛል የደስታ ነው ቤቴ
እፎይታ ሆኖልኝ በኢየሱስ አባቴ
አዝማች · Chorus
ላመስግንህ እጆቼን አንስቼ
ላመስግንህ በፊትህ ወድቄ
ላመስግንህ ጌታ ላመስግንህ
ላመስግንህ ኢየሱስ ላመስግንህን
ቁጥር 3 · Verse 3
ላመስግንህ ላመስግንህ
ልዘምርልህ ላመስግንህ
ሞኝነት አይደለም ለእርሱ መዘመሬ
ነፍሱን ሰጥቶኝ ነው በሕይወት መኖሬ
ታዲያ ላመስግነው የምን ዝምታ ነው
ለወደደኝ ጌታ የፍቅር ቅኔ ነው
አዝማች · Chorus
ላመስግንህ እጆቼን አንስቼ
ላመስግንህ በፊትህ ወድቄ
ላመስግንህ ጌታ ላመስግንህ
ላመስግንህ ኢየሱስ ላመስግንህን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ