እንደ እግዚአብሔር ያለ
Ende Egziabhier Yale
2012 · ትራክ 12 · 5:53 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አይዞህ ባይ ሲጠፋ የሚቆም ከጐኔ
የልቤን ተረድቶ እንባ የሚያብስ ከዓይኔ (፪x)
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ትናንትና እንዴት ይታለፍ
ጭንቅ ነበር ለብቻ ሲታሰብ
በዙሪያዬ ጠላት ከቦኝ
ማን ያድነኝ ብዬ ተረበሽኩኝ
ሰማያት ተከፈቱና
በተከበበው ከተማ
ምህረቱን አበዛልኛ (፪x)
ዛሬም ከእኔ ጋራ ነህ (፮x)
አዝማች · Chorus
አይዞህ ባይ ሲጠፋ የሚቆም ከጐኔ
የልቤን ተረድቶ እንባ የሚያብስ ከዓይኔ (፪x)
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስደክምበት ዞር በይ ደካማ
አላለኝ ደግ ነው ጌታ
አቅም ሆነ ኃይል አስታጠቀኝ
በከፍታ ላይ አቆመኝ
ሰማያት ተከፈቱና
በተከበበው ከተማ
ምህረቱን አበዛልኛ (፪x)
ዛሬም ከእኔ ጋራ ነህ (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ