ለምን
Lemen
2012 · ትራክ 5 · 6:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በጊዜያዊው ነገር ልቤ እንዳይሸነፍ
በሚያልፈው ነገር ነፍሴ እንዳትታለፍ
ቃልህን በልቤ ሰውረው ጌታዬ
ትዛዝህን ልጠብቅ
ማስተዋል ይሁነኝ ወዳጄ
አዝማች · Chorus
ጥበብህ ትሁነኝ እህቴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያንተውማ ነገር ለምን ይይዘኛል
የሚያልፈው ነገር ለምን ያታልለኛል
ከንቱውማ ነገር ለምን ይይዘኛል
የሚያልፈው ነገር ለምን ያታልለኛል
አዝማች · Chorus
ለምን ለምን አሄሄ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ትላንትና የናቁትን
ከንቱ ብዬ ያጥላላሁትን
ዛሬ ደግሞ ልወዳጀው
ለምንድን ነው እንዲህ
አዝማች · Chorus
ፍቅር/ጓደኛ እምሆን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ባሞግስህ ደግሞ መልሶ ሲያሟግ
ባከበርህ ደግሞ ሲያማርርብኝ
ክፉ ደጉን ሁሉ እየተናገረ
ይሄ አንደበቴ አንተን አስመረረ
በአንደበቴ ላክብርህ
አዝማች · Chorus
ደስ የሚልህን ልናገርልህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ያምራል ስባል ሞት ነው ብዬ
ትናንትናን ንቄው ዘግቼው አልፌ
ዛሬ ደግሞ ምን ተገኝቶ
የናቁትን ማየት ኋላ ተመልሶ
በአደባባይ ላይ ቆሜ ላመልክህ
ከቅዱሳን ጋራ ሆኜ በፊትህ
ያልሆንኩትን ሆኜ በሰው ፊት ስታይ
መጥፊያዬ እንዳይሆን የምልህ አለኝ
በጓዳዬ ሆኜ ላክብርህ
ሰው ያላየው ባህሪዬ ያስደስትህ
በጓዳዬ ሆኜ ላክብርህ
ድብቅ ገመናዬ ያስደስትህ
አዝማች · Chorus
እኔ በቃኝ (፪x) መሸነፍ በቃኝ
እኔ በቃኝ (፪x) መታለል በቃኝ
አዎ በቃኝ (፪x) መታለል በቃኝ
አዎ በቃኝ (፪x) መሸነፍ በቃኝ
ቁጥር 6 · Verse 6
በቃ በል እስቲ ጣልቃ ግባና
ሁሉ የሚያምረው በአንተ ነውና
በቃሽ በለኝ ጣልቃ ግባና
ሁሉ የሚሳካው በአንተ ነውና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ