እንደገና
Endegena
2012 · ትራክ 13 · 4:33 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እንደገና በብዙ ምህረትህ ይቅር አልከኝ
እንደገና በብዙ ይቅርታህ አከበርከኝ
እንደገና እንደገና አሄ እንደገና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ ኃጢአት ብዛት አልፈረከብኝ
እግዚአብሔር ምህረቱን አልከለከለኝ
በፊቱ ወድቄ ምህረት ባልኩበት
ይቅርታ በዝቶልኝ ይኸው ዘመርኩለት
አዝማች · Chorus
እንደገና በብዙ ምህረትህ ይቅር አልከኝ
እንደገና በብዙ ይቅርታህ አከበርከኝ
እንደገና እንደገና አሄ እንደገና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሊከሱኝ ወደው ኃጢአተኛ ብለው
በድንጋይ ሊወግሩኝ ዳኛ ፊት አቅርበው
የተገባኝን ሞት አይገባም ብሎ
ምህረት አረገልኝ ሀፍረቴን ከልክሎ
አዝማች · Chorus
እንደገና በብዙ ምህረትህ ይቅር አልከኝ
እንደገና በብዙ ይቅርታህ አከበርከኝ
እንደገና እንደገና አሄ እንደገና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የምህረት አምላክ ደጁ ተከፈተ
ለብዙ በደሌ ይቅርታ . (1) .
እንደገና ቆሜ ፊቱ ዘምራለሁ
የማረኝን አምላክ አመሰግናለሁ
አዝማች · Chorus
እንደገና በብዙ ምህረትህ ይቅር አልከኝ
እንደገና በብዙ ይቅርታህ አከበርከኝ
እንደገና እንደገና አሄ እንደገና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ