እኔን ለክብር
Enien Lekeber
2012 · ትራክ 6 · 5:39 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔን ለክብር ለሽልማት ያበቃኝ
እግዚአብሔር ከትቢያ ላይ አነሳኝ (፪x)
በሰው ዓይንም አልሞላ
ነኝ እኮ ደካማ
ግን እኔ ማን ነኝ የተወደድኩኝ
በእግዚአብሔር የተመረጥኩኝ (፪x)
ከሰው ተራ የሚያድን መልካም ነገር የለኝ
ጐሽ የእኔ ልጅ ተብሎ የሚያስመሰግን
ምህረትህና ፍቅርህ ሰው አድርገውኛል
ከቅዱሳን ጋራ ያዘምሩኛል
አዝማች · Chorus
ተሰጥቼ ፊትህ ሆኜ እኔ ባመልክህ
ያንስብሃል ለውለታህ ሲታሰብ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርቃንህን አደባባይ እንደ ወንጀለኛ
ምንም ሳታጠፋ ስለ እኔ ተገፋህ
ያ ሁሉ ልፋትህ እኔን ለማዳን ነው
ከክብርህ ወርደህ ዝቅ ዝቅ ያልከው
አዝማች · Chorus
ተሰጥቼ ፊትህ ሆኜ እኔ ባመልክህ
ያንስብሃል ለውለታህ ሲታሰብ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔን ለክብር ለሽልማት ያበቃኝ
እግዚአብሔር ከትቢያ ላይ አነሳኝ (፪x)
በሰው ዓይንም አልሞላ
ነኝ እኮ ደካማ
ግን እኔ ማን ነኝ የተወደድኩኝ
በእግዚአብሔር የተመረጥኩኝ (፪x)
ሰው ሰውን የሚወደው በእራሱ ምርጫ ነው
ድካም ያለበትን ማነው የሚቀበለው
አንተ ግን ስትወደኝ ስትቀበለኝ
ደካማ ነሽ ብለህ ፊትህን አልነሳኸኝ
አዝማች · Chorus
ተሰጥቼ ፊትህ ሆኜ እኔ ባመልክህ
ያንስብሃል ለውለታህ ሲታሰብ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ