ላሰናዳው ቤቴን
Lasenadaw Bietien
2012 · ትራክ 10 · 6:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይመጣል ኢየሱስ
ኢየሱስ ይመጣል
በታላቅ ብርሃን ተገልጦ መልአኩ
አዋጅ ነገራቸው ለእረኞች ሁሉ
ንጉሥ ተወለደ በቤተልሔም ከተማ
ሄዳችሁ ስገዱ በግርግም አለና (፪x)
መላዕክት ያወጁለት እረኞች የሰገዱለት
አዝማች · Chorus
ይሄ ወዳጄ ድንገት ይመጣል
እንዳልቀር ከደጅ ላሰናዳው ቤቴን (፪x)
ላሰናዳው ቤቴን
ንፁህ ላድረገው ሕይወቴን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ላሰናዳው ቤቴን
ኢየሱስ ይመጣል
ኢየሱስ ይመጣል
በቃላ ገሊላ ጀመረ ተዓምሩ
የአባቱን ፈቃድ ፈፀመ ትዕዛዙን
ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት በመስቀል የሞተው
ኢየሱስ ይመጣል ቤቴን ላሰናዳው
አዝማች · Chorus
ይሄ ወዳጄ ድንገት ይመጣል
እንዳልቀር ከደጅ ላሰናዳው ቤቴን
ላሰናዳው ቤቴን
ንፁህ ላድረገው ሕይወቴን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔስ ልሁን ከልባሞቹ
መቅረዜን ልሙላ አላንቀላፋ
ድንገት ሲመጣ ይኼ ወዳጄ
እንዳልቀር ኋላ ካሁኑ ልንቃ
አዝማች · Chorus
ይሄ ወዳጄ ድንገት ይመጣል
እንዳልቀር ከደጅ ላሰናዳው ቤቴን
ላሰናዳው ቤቴን
ንፁህ ላድረገው ሕይወቴን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የምድሩ ክብር ዝናው
ሲደምቅልኝ አቤት ጭብጨባው
ሞቅ ብሎ እንዳልዘነጋ
ተይ ነፍሴ ሙግትሽህ ምንድን ነው
አይግረምሽ አይድነቅሽ
መዝገብም አይሆን ለላይኛው ቤቴ
ተይ ተይኝ ነፍሴ ተይኝ
ከአምላክሽ ጋራ ተስማሚልኝ
የሚረባን የሚያውቅ እርሱ አይደለም ዎይ
የሚበጅሽንስ እርሱ አይደለም ዎይ
በቃ ተይኛ ነፍሴ ተይኝ
ከአምላክሽ ጋራ ተስማሚልኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ