ማልጄ ልነሳ
Malejie Lenesa
2012 · ትራክ 4 · 3:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠላቴ ብዙ ብዙ ይጮሃል
ጆሮም አልሰጠው ይደክማል
ለእኔ የሆነልኝ እንደዚህ ነው
የዜማ ጊዜ ደርሶ ወይን አብቦልኝ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል
ጌታውን የጠበቀ ይከብራል
ከአምላኩን ተማምኖ የከሰረ የታል
በጊዜው ሰዓቱ ሁሉ አምሮለታል (፪x)
አዝማች · Chorus
ማልጄ ልነሳ ከበሮዬን ላንሣ
አምላኬን ላመስግን ላሰማ የድል ዜማ
አስጨናቂው ለሊት አልፎልኛል
ኢየሱስ ብርሃኔ በርቶልኛል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ውሎ የማድር ብሆን ከንጉሥ ደጅ አፍ
ክፉ የሚታሰበ ከንጉሥ ወዳጅ
ጌታውን ለጠበቀ ነገሩ ተገለበጠ
በክፉው ምክር ላይ እግዚአብሔር ተገለጠ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማልጄ ልነሳ ከበሮዬን ላንሣ
አምላኬን ላመስግን ላሰማ የድል ዜማ
አስጨናቂው ለሊት አልፎልኛል
ኢየሱስ ብርሃኔ በርቶልኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ