እግዚአብሔር ሲናገር
Egziabhier Sinager
2012 · ትራክ 11 · 3:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሚገርመኝ እኔ ቅጥሩ ታላቅ ነው
ማንም እንዳይነካኝ ለእኔ ያሰበው
ተዘልለሽ ኑሪ እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ
ለምን ትፈሪያለሽ . (1) .
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሲናገር
ሰማሁ ተነሳሁ
እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ
ሰላም ኑሪ አለኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔን የሚጠብቅ አይተኛ አያንቀላፋ
ይልቁን በእሳቱ ጠላቴን አጠፋ
ክንዱ ተዘርግታ አርፌ በጌታ
ሳልሰጋ ኖራለሁ ሁልጊዜም በደስታ
እርግማን እንዳይሰራ በዘመኔ
ሟርትም እንዳይሰራ በዘመኔ
ቅጥር ሆንከኝ መድህኔ (፫x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሲናገር
ሰማሁ ተነሳሁ
እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ
ሰላም ኑሪ አለኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የጠላቴን ምክር ዛቻውን እንዳልፈራ
በእሳት የሚመልስ አለኝ የሚያኮራ
ዙሪያዬ ቢዞር ጠላት ቢጮህ
መናወጥ አላውቅ ሰላሜ አይጠፋ
እግዚአብሔር ብሎኛል ልጄ እረፊ
በዘመንሽ ሁሉ ሰላም ለአንቺ
ሰላም ይሁን ከቤትሽ (፫x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሲናገር
ሰማሁ ተነሳሁ
እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ
ሰላም ኑሪ አለኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ