በሌሊትም
Belielitem
2007 · ትራክ 12 · 5:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሌሊትም ከልቤ ጋር ተጫወትኩኝ
ነፍሴንም አነቃቃኋት ጌታን አሰብኩኝ
እርሱን ሳስብ ልቤ በደስታ ሁሌ ይሞላል
ያስጨነቀኝንም ሁሉ ጌታ ይጥላል
እግዚአብሔርን ሳየው ደስ አለኝ
እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስ አለኝ
አዝማች · Chorus
እርሱን ተመልከቱ ያበራላችኋል (፪x)
የጨለመውንም ጌታ ይገፈዋል (፪x)
ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችኋል
የጨለመውንም ጌታ ይገፈዋል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለተጨነቀ ሰው ጨለማ አይሆንም ብሏል
በእውነት ለሚታመኑት ልቡ ይራራል
አሁንም ተስፋዬም ትዕግሥቴም በእርሱ ነው
በዘመኔ እያሰብኩት እደሰታለሁ
እግዚአብሔርን ሳየው ደስ አለኝ
እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስ አለኝ
አዝማች · Chorus
እርሱን ተመልከቱ ያበራላችኋል (፪x)
የጨለመውንም ጌታ ይገፈዋል (፪x)
ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችኋል
የጨለመውንም ጌታ ይገፈዋል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ስትፈለግ የምትገኝ አንተ ነህ
ምታጽናና ምትደግፍ ወዳጅ ነህ
በብርሃንህ ብርሃን እንዳይ አደረከኝ
በቀረብኩህ ቁጥር ጌታ አበራህልኝ
አንተ ሙሉ ነህ እታመንሃለሁ
ዓይኔን ከሰው ላይ ይኸው አንስቻለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ ብቻህን በቂ ነህ አንተ ብቻህን (፪x)
አንተ ብቻህን ሙሉ ነህ አንተ ብቻህን (፪x)
አንተ ሙሉ ነህ እታመንሃለሁ
ዓይኔን ከሰው ላይ ይኸው አንስቻለሁ
አንተ ብቻህን በቂ ነህ አንተ ብቻህን (፪x)
አንተ ብቻህን ሙሉ ነህ አንተ ብቻህን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ