እንደወደድከኝ አወኩ
Endewededkegn Aweku
2007 · ትራክ 11 · 8:31 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሥጋናን የሚሰዋ ያከብረኛል ያከብረኛል ብለሃል
እሰዋለሁ ምሥጋናዬ ይኸው
እሰዋለሁ አምልኮዬ ይኸው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምሥጋናን በአፌ የጨመርክ
ምሬትን ከእኔ ያስወገድክ
አምላኬ አንተ ነህና
ይብዛልህ ዛሬም ምሥጋና
ይገባሃልና አሜን ይገባሃልና
አዝማች · Chorus
እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
ከዙፋንህ ስርም እንሰግድልሃለን
እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
በእውነት በመንፈስ እንሰግድልሃለን
ቁጥር 3 · Verse 3
ክብርህን ላውራ ጌታዬ
ሞገስ ያግኝ ምሥጋናዬ
ሳከብርህ ሁሌ ደስ ይለኛል
እረካለሁ ክብርህ ያጠግበኛል
ክብርህ ያጠግበኛል አሜን ክብርህ ያጠግበኛል
አዝማች · Chorus
እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
ከዙፋንህ ስርም እንሰግድልሃለን
እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
በእውነት በመንፈስ እንሰግድልሃለን
ቁጥር 4 · Verse 4
ድል በመንሳቱ ለሚያዞረኝ
በጠላቶቼ ዕራስ ላይ ላቆመኝ
እዘምራለሁ ለጌታ እዘምራለሁ አሃ
እዘምራለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ ኦሆ
ያስጨናቂውን ዘንድ ጌታዬ ሰባበርከው
ግዙፉን ቀንበሬን ከላዬ አስወገድከው
ሁሌ እደነቃለሁ ጌታዬ በማዳንህ
ባለህ ምሥጋና ላይ ሌላም ልጨምርልህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ዝናህን አወራለሁ (፫x) ማዳንህን እናገራለሁ
ዝናህን አወራለሁ (፫x) ማዳንህን እናገራለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
ጣላቴ ይዞራል የሚውጠው ፈልጐ
ምንም ላይሞላለት ሁሌ መናውን ቀርቶ
እኔን ግን ጌታዬ ከድል ድል ያዞረኛል
ጠላቴን ከእግሬ ስር ጌታዬ አስረግጦኛል (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ጠላቴ ዕልል አይልብኝምና
እንደወደድከኝ አወቅሁ
እንደመረጥከኝ አወቅሁ (፪x)
በእኔ ድንኳን ዕልልታ ይሰማዋል ዝማሬ ይሰማዋል
የወደደኝ ጌታ ይህንን አድርጓል
የመረጠኝ እርሱ ይህንን አድርጓል
ቁጥር 7 · Verse 7
የማንም ባለዕዳ ያልሆነው እግዚአብሔር
አፈራረሰና የጠላቶቼን ምክር
አዳዲስ ዝማሬ በአፌ ውስጥ ሲጨምር
የነፍሴ ቅኝቷ ሁሌ ክብር ክብር (፪x)
አዝማች · Chorus
ዝናህን አወራለሁ (፫x) ማዳንህን እናገራለሁ
ዝናህን አወራለሁ (፫x) ማዳንህን እናገራለሁ
ቁጥር 8 · Verse 8
ክበር ከሚሉህ ጋር ፤ ንገሥ ከሚሉህ ጋር (፪x)
እስማማለሁ እኔም እጨምራለሁ (፬x)
ክበር ከሚሉህ ጋር ፤ ንገሥ ከሚሉህ ጋር (፪x)
እስማማለሁ እኔም እጨምራለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ