ቃልህን እወደዋለሁ
Qalehen Wededkut
2007 · ትራክ 2 · 4:44 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው
በቃልህም ልቤን ደስ አለው
የደስታዬ/የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ
መተኪያና እኩያ የለህ (፪x)
ቃልህን እወደዋለሁ (፪x)
ድምጽህን እወደዋለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የእግዚአብሔር ቃሉ የነጠረ ነው
ለሚታመኑበት እርሱ ጋሻ ነው
ለቃልህ ጌታዬ እኔም እገዛለሁ
ሁኚ ያለኝን ሁሉ ዛሬም እሆናለሁ
ያፅናናኝን የደረሰልኝን
በመንገዴ ሁሌ የሚመራኝን
ሕይወቴንም ለቀየረልኝ
ቃልህ ብቻ ሁሌ አስተማማኝ
አዝማች · Chorus
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው
በቃልህም ልቤን ደስ አለው
የደስታዬ/የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ
መተኪያና እኩያ የለህ (፪x)
ቃልህን እወደዋለሁ (፪x)
ድምጽህን እወደዋለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአፍህ የሚወጣው ሕያው የአንተ ቃል
መሻት ግን ወደ እኛ ስቦ ያመጣል
ያድናል ይገላል ይተክላል ይነቅላል
እርሱ ያለው ብቻ በእርግጥም ይሆናል
ሳር ይደርቃል አበባው ይረግፋል
በምድር ያለው ሁሉ ይለዋወጣል
ዘመን ጊዜ የማይለዋውጠው
የአምላኬ ቃል ፀንቶ የሚኖር ነው
አዝማች · Chorus
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው
በቃልህም ልቤን ደስ አለው
የደስታዬ/የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ
መተኪያና እኩያ የለህ (፪x)
ቃልህን እወደዋለሁ (፪x)
ድምጽህን እወደዋለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ