ወጀቡ
Wejebu
2007 · ትራክ 1 · 7:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተን የታመነ መች አፈረ
አንተን የታመነ መች ከሰረ
አምላኬ ሆይ ብርቱ መታመኛዬ ነህ
ኢየሱሴ ብርቱ መታመኛዬ ነህ
አምላኬ ሆይ ብርቱ መታመኛዬ ነህ
ኢየሱሴ ብርቱ መታመኛዬ ነህ (፪x)
ትላንትን አልፌ ዛሬ ደርሻለሁ
ደርሻለሁ ዛሬ ደርሻለሁ (፪x)
ቀኝህ ደግፎኛል ለነገ አምንሃለሁ
አምንሃለሁ ለነገ አምንሃለሁ (፪x)
ምን ያስደነግጣል ለምን እሰጋለሁ
እሰጋለሁ ለምን እሰጋለሁ (፪x)
ተሻገሪ ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋር ነው
ከእኔ ጋር ነው ጌታ ከእኔ ጋር ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አለ ፣ አለ አለ
አምላኬ አለ ፣ አለ አለ
በኃይሉ አለ ፣ አለ አለ
በሥራው አለ ፣ አለ አለ
እኔም አየሁት ፣ አለ አለ
ሲደርስልኝ ፣ አለ አለ
ጠላቴን ረግጦ ፣ አለ አለ
ሲወጋልኝ ፣ አለ አለ
ቁጥር 2 · Verse 2
ወጀቡ ቢበዛ ነፋሱ ቢያይልም
ኦ ቢያይልም ነፋሱ ቢያይልም (፪x)
ቃሉን እይዛለሁ አልነቃነቅም
አሃ አልነቃነቅም (፪x)
ቃል ይናገር እንጂ ቃሉን የሚጠብቅ
አሃ ቃሉን የሚጠብቅ (፪x)
ከሁኔታ በላይ አምላኬ ነው ትልቅ
አሃ አምላኬ ነው ትልቅ (፪x)
ክበር ዛሬ እንደገና (፫x)
ልርካ ክብርህን ልይና
ልጥገብ ክብርህን ልይና
ልጥገብ ክብርህን ልይና (፪x)
ለፈተና መውጫ አዘጋጀልኝ
አሃ አዘጋጀልኝ (፪x)
ለማዕበሉ ደግሞ ገደብ ሰራልኝ
አሃ ገደብ ሰራልኝ (፪x)
የእኔ ነገር እርሱን ይመለከተዋል
አሃ ይመለከተዋል (፪x)
ስለ እኔ ተዋግቶ አሸንፎልኛል
አሃ አሸንፎልኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አለ ፣ አለ አለ
አምላኬ አለ ፣ አለ አለ
በኃይሉ አለ ፣ አለ አለ
በሥራው አለ ፣ አለ አለ
እኔም አየሁት ፣ አለ አለ
ሲደርስልኝ ፣ አለ አለ
ጠላቴን ረግጦ ፣ አለ አለ
ሲወጋልኝ ፣ አለ አለ
ቁጥር 3 · Verse 3
የዮርዳኖስ ጩኸት ዝም ብሎ እያጓራ (፫x)
አምላክን ጥራ እንጂ አትደንግጥ አትፍራ (፫x)
ዮርዳኖስ ፉከራው እስክትረግጠው ነው (፫x)
አይዞህ በእምነት ግባ ያዘዘህ ጌታ ነው (፫x)
ክበር ዛሬ እንደገና (፫x)
ልርካ ክብርህን ልይና
ልጥገብ ክብርህን ልይና
ልጥገብ ክብርህን ልይና (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ