ለእኔ ግን
Lenie Gen
2007 · ትራክ 9 · 6:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሚሰማ ግን በእርጋታ ይቀመጣል
ከመከራ ከጭንቀት ከሥጋት ያርፋል
ጌታዬ እሰማሃለሁ ከጭንቀት ከሃዘን አርፋለሁ (፪x)
ብለሃል እሰማሃለሁ ከጭንቀት ከሃዘን አርፋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ለእኔ ግን ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሚያስፈልገው ጥቂት አንድ ነው (፪x)
በእግርህ ስር ሆኖ አንተን ማድመጥ ነው (፪x)
ይህን ተረዳሁ ምን እፈልጋለሁ (፪x)
ከእግርህ ስር ሆኜ አደምጥሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ለእኔ ግን ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከዝማሬዬ ይልቅ ኑሮዬ ያክብርህ (፪x)
በሕይወት ዘመኔ ስንቱን ላስጠራልህ (፪x)
ከአገልግሎቴ ይልቅ ሕይወቴ ያማረ ይሁን (፪x)
አንተ እንደምትወደው እንደፈቀድክ ይሁን (፪x)
አዝማች · Chorus
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ለእኔ ግን ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታዬ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ (፪x)
ፊትህንም ማየት እጅግ ናፍቃለሁ (፪x)
የሚረዳኝ ፀጋ ከአንተ ፈልጋለሁ (፪x)
ስለዚህ ጌታዬ ወደ አንተ እቀርባለሁ (፪x)
የሚሰማ ግን በእርጋታ ይቀመጣል
ከመከራ ከጭንቀት ከሥጋት ያርፋል
ጌታዬ እሰማሃለሁ ከጭንቀት ከሃዘን አርፋለሁ (፪x)
ብለሃል እሰማሃለሁ ከጭንቀት ከሃዘን አርፋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ድምጽህን አሰማኝ ጌታዬ ድምጽህን አሰማኝ
ለእኔ ግን ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ