ደርቤ
Derebie
2007 · ትራክ 8 · 5:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ደርቤ ደርቤ ላብዛው ምሥጋናዬን
ለምወደውና ለቸሩ ጌታዬ
ምሥጋና ይብዛልህ አሃሃ
አምልኮና ክብር ኦሆሆ
ይሄ ነው መሻቴ አሃሃ
አንተን እንዳስከብር ኦሆሆ
አዝማች · Chorus
የልቤ ናፍቆት ስትከብር ማየት ነው
አቤቱ አመሰግንሃለሁ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሕይወቴ ብርሃን ብርሃን ይሁን ያልከው
እግዚአብሔር ተባረክ በሰማይ ያለኸው
ከክብር ጋር ጌታ አሃሃ
ተቀብለኸኛል ኦሆሆ
ከፊትህ ጋር ደስታን ኣሃሃ
አንተ አጥግበኸኛል ኦሆሆ
አዝማች · Chorus
የልቤ ናፍቆት ስትከብር ማየት ነው
አቤቱ አመሰግንሃለሁ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከጠላት መንጋጋ ያወጣኝ ፈልቅቆ
የምኖርበትን አይቶታል አርቆ
የክብሩ ፀዳል አሃሃ
በእኔ ላይ በራልኝ ኦሆሆ
ያስጨነቀኝ ሁሉ አሃሃ
በረከት ሆነልኝ ኦሆሆ
አዝማች · Chorus
የልቤ ናፍቆት ስትከብር ማየት ነው
አቤቱ አመሰግንሃለሁ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የልቤ ናፍቆት ስትከብር ማየት ነው
አቤቱ አመሰግንሃለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ