ይህን ያረገው
Yehen Yaregew
2007 · ትራክ 13 · 4:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወደ ፀጋህ ዙፋን በእምነት እቀርባለሁ ፤ በእምነት እቀርባለሁ
በኢየሱስ ምክንያት ድፍረት አግኝቻለሁ ፤ ድፍረት አግኝቻለሁ (፪x)
የከበደው ኪዳን ይኸው ቀለለልኝ ፤ ይኸው ቀለለልኝ
በነጻ እንዳመልከው ልጁን ሰደደልኝ ፤ ልጁን ሰደደልኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይህን ያረገው (፪x) ይህን ያረገው ጌታዬ እንዳመልከው ነው
ይህን ያረገው (፪x) ይህን ያረገው ጌታዬ እንዳመልከው ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
በግ : እርግብ አልይዝም አንተን ለማምለክ ፤ አንተን ለማምለክ
እንጨት ረብርቤ እሳት አላነድም ፤ እሳት አላነድም (፪x)
ያንን ከባድ ስርዓት ኢየሱስ አስቀረው ፤ ጌታዬ አስቀረው
ያለምንም ድካም እርሱን እንዳመልከው ፤ እርሱን እንዳመልከው አዎ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይህን ያረገው (፪x) ይህን ያረገው ጌታዬ እንዳመልከው ነው
ይህን ያረገው (፪x) ይህን ያረገው ጌታዬ እንዳመልከው ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
በፍፁም ልቤ በፍፁም ሃሳቤ
ጌታን እወደዋለሁ ከሁሉም አብልጬ (፪x)
አብልጬ ከሁሉም አስበልጬ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ