ቅዱስ
Qedus
2007 · ትራክ 4 · 5:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቅዱስ (፫x) እግዚአብሔር (፪x)
በታላቅ ብርሃን በክብር ያለህ
ግርማህ አስፈሪ መሳይ የሌለህ
ፍጥረት በፊትህ ይንቀጠቀጣል
ክብርህን አይቶ ማን ሰው ይቆማል?
ቅዱስ (፫x) እግዚአብሔር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በፈቃዴ ደስ እያለኝ ጌታ አመልክሃለሁ (፬x)
አምላክ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ክበር ጌታ (፬x)
ንጉሥ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ንገሥ ጌታ (፬x)
ስለአንተ በየዕለቱ መደነቅ ሞልቶኛል
ዛሬም መንፈስ ቅዱስ አምልኪው ይለኛል
ለምን እንደምኖር ምክኒያቱ ገብቶኛል
አንተን ለማምለክ ነው እኔም ተስማምቶኛል
በመፍራት በመንቀጥቀጥ በፊትህ እቀርባለሁ
ክብር ለሚገባህ ለአንተ ክብርን እሰጣለሁ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ይገባሃል ክብር
አምላኬ ይገባሃል
አምላኬ ይገባሃል ስግደት
አምላኬ ይገባሃል (፪x)
አምላክ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ክበር ጌታ (፬x)
ንጉሥ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ንገሥ ጌታ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አምላክ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ክበር ጌታ (፬x)
ንጉሥ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ንገሥ ጌታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ