Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ትበቃኛለህ

Tebeqagnaleh

2007 · ትራክ 5 · 5:07 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከሆነልኝ ነገር ሁሉ ይልቅ

ያረከው አንተ ሆንክልኝ ድንቅ (፪x)

ስለዚህ ትበቃኛለህ

ሁልጊዜ ታስመካኛለህ (፪x)

የከበደኝን ሁሉ አንተ አቀለልከው

ፀሎቴንም እየሰማህ ጥያቄዬን መለስከው

ለሰው ልጆች መልካምን በማድረግ ደስ ይልሃል

ልዩ ነህ የእኔ ጌታ ማንስ ይመስልሃል

ስለዚህ ትበቃኛለህ

ሁልጊዜ ታስመካኛለህ (፪x)

በዕድሌ እኮ አይደለም በደረሰኝ እጣ

ምታኖረኝ እግዚአብሔር ነህ ሁሌ ባለጠጋ

በክንዶችህ ተማምኜ በጥላህ አድራለሁ

ጥጋቤ ነህ እርካታዬ አርፌብሃለሁ

ስለዚህ ትበቃኛለህ

ሁልጊዜ ታስመካኛለህ (፪x)

በልቤ ውስጥ ያለው ሞልቶ የፈሰሰው (፪x)

በውስጤ ያረከው የፍቅር እሳት ነው (፪x)

ይህንን አይቼ እንዴት ዝም እላለሁ (፪x)

በአዲስ በአዲስ ዜማ አመሰግናለሁ (፪x)

የእኔ ጌታ ተባረክልኝ (፫x)

ሌላማ ምን እልሃለሁ ተባረክልኝ (፪x)

ሰልፉን ለአንተ ሰጠሁ እኔ እቆማለሁ (፪x)

ቸርነት ምህረትህን ሁሌ እናገራለሁ (፪x)

ድብቅ ጦር አንስተህ ጠላቴን መተሃል (፪x)

ድል አድራጊው ኢየሱስ ክብር ይገባሃል (፪x)

የእኔ ጌታ ተባረክልኝ (፫x)

ሌላማ ምን እልሃለሁ ተባረክልኝ (፪x)

ታማኝነትህን ሁሌ አወራለሁ

ቸርነትህን ዘለዓለም ዘምራለሁ (፪x)

ሌላማ ምን እልሃለሁ ጌታዬ

ሳከብርህ ያኔ ረካለሁ አምላኬ (፪x)

ታማኝነትህን ሁሌ አወራለሁ

ቸርነትህን ዘለዓለም ዘምራለሁ (፪x)

ሌላማ ምን እልሃለሁ ጌታዬ

ሳከብርህ ያኔ ረካለሁ አምላኬ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ