ቤት አለኝ
Biet Alegn
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቤት አለኝ ቤት አለኝ ቤት (፪x)
ስገባበት ኦሆ እርፍ ምልበት
በሰማይ አለኝ ቤት
አዝማች · Chorus
የሰማዩን ቤቴን ሳስበው
ይገርመኛል እደነቃለሁ
እንደምድሩ አላፊ አይደለ
ጸንቶ ሚኖር እጅግ ያማረ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰው እጅ ጭራሽ ያልነካው
ከአይምሮ በላይ የሆነው
አምላኬ እራሱ የገነባው
የምድር ሃብት ቢከማች የማይተካው
አዝማች · Chorus
የሰማዩን ቤቴን ሳስበው
ይገርመኛል እደነቃለሁ
እንደምድሩ አላፊ አይደለ
ጸንቶ ሚኖር እጅግ ያማረ
ቁጥር 3 · Verse 3
ችግርን የማላይበት
ሃዘን ለቅሶ ከቶ የሌለበት
አምላኬ ሚመለክበት
ዘለዓለም እኔም ማርፍበት
አዝማች · Chorus
የሰማዩን ቤቴን ሳስበው
ይገርመኛል እደነቃለሁ
እንደምድሩ አላፊ አይደለ
ጸንቶ ሚኖር እጅግ ያማረ
ቁጥር 4 · Verse 4
ምንኛ እድለኛ ነኝ
የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሽ ነኝ
አልሰጋም ምን እሆን ብዬ
ዋስትና ስላለኝ ብዬ
አዝማች · Chorus
የሰማዩን ቤቴን ሳስበው
ይገርመኛል እደነቃለሁ
እንደምድሩ አላፊ አይደለ
ጸንቶ ሚኖር እጅግ ያማረ
ቁጥር 5 · Verse 5
ና ኢየሱስዬ ናልኝ
ና ኢየሱስዬ ና ናልኝ
በጣም ናፈቅከኝ እጅግ ናፈቅከኝ
በጣም ናፈቅከኝ እጅግ ናፈቅከኝ (፪x)
በጣም ናፈቅከኝ እጅግ ናፈቅከኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ