ኢትዮጵያ
Ethiopia
2011 · ትራክ 13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢትዮጵያ (፬x)
ስንጮህ ስናለቅስ ሳይሰማው ቀርቶ
አይደል ላለማገዝ ላለመርዳት ብሎ
አሁን ምናየውን ዳግም እንዳናየው
እስከመጨረሻ ሊቀብረን ሊያስቀረን
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ መከራሽ እንደዚህ የበዛው
ጨለማው እንዲህ የበረታው
የኢየሱሴ ስራ ይገለጥ ዘንድ ነው
ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ
ልትጠፊ አይደለም ልትዋረጂ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢትዮጵያ (፬x)
ዛሬ የሚቀመስ ምንም ነገር ሳይኖር
ነገ ይጠገባል ተርፎ ይሸጣል ቢለን
የችግሩ ብዛት ግራ ቢያጋባንም
ቃል ወጥቷል ከሰማይ መሆኑ አይቀርም
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ መከራሽ እንደዚህ የበዛው
ጨለማው እንዲህ የበረታው
የኢየሱሴ ስራ ይገለጥ ዘንድ ነው
ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ
ልትጠፊ አይደለም ልትዋረጂ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰው ደመናን አይቶ ሊዘንብ ነው ይላል
አምላኬ በራሱ ተማምኖ ያወራል
ተስፋ ገብቶላታል ላለሁባት ምድሬ
እኔ እርግጠኛ ነኝ ታየዋልች ህልሜን
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ መከራሽ እንደዚህ የበዛው
ጨለማው እንዲህ የበረታው
የኢየሱሴ ስራ ይገለጥ ዘንድ ነው
ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ
ልትጠፊ አይደለም ልትዋረጂ
ቁጥር 4 · Verse 4
የኢትዮጵያን መባረክ አትጠራጠሩ
ይሄ በተአምር አይሆንም አትበሉ
እግዚአብሔር አለ ሆነ ነው በቃሉ
እርሱ እውነተኛ አይዋሽም እመኑ
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ መከራሽ እንደዚህ የበዛው
ጨለማው እንዲህ የበረታው
የኢየሱሴ ስራ ይገለጥ ዘንድ ነው
ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ
ልትጠፊ አይደለም ልትዋረጂ
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢትዮጵያ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ