ቀደም ቢል ምን አለ
Qedem Bil Men Ale
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወይ አለማወቄ መጠንከሩ ልቤ
የተረኩልኝን ይዤ አለቅ ማለቴ
እምነት ከመስማት ነው መስማትም በቃሉ
እንደተንተራስኩት ዘመን ተቆጠሩ
ፀሐይ ስትጠልቅ ጥላው ሲሸሽም ማታ
ጉብዝናው ካለፈ ቢደርስልኝ ጌታ
አዝማች · Chorus
ባለኝ ይሄ መልካም ነገር
ቀደም ቢል ምን አለ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጥርስ ከነቀልኩበት ከአደኩበት ቤቴ
አልለይም እያልኩ ከእናት ከአባቴ
ይማህተም ለውጥ የማደርግ መስሎኝ
ለካ የመንግሥት ነው ይሄ መቼ ገብቶኝ
ወደ እግዚአብሔር ግዛት ፈቅጄ ብገባ
ሰብሮ ቢያላቅቀኝ ከዚያ ከጨለማስ
አዝማች · Chorus
ባለኝ ይሄ መልካም ነገር
ቀደም ቢል ምን አለ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መናኛውም ከፊት መልካሙም ከኋላ
እንዲሁ በደመነፍስ ነበር የኔ ስራ
ከዛ ተረት ተረት ሕይወት ውስጥ አውጥቶ
መንገድ ቢያስጀምረኝ ትርጉም ላለው ኑሮ
ቃሉ ቢጣፍጠኝ እንደ ማር ወለላ
ልቤን ዘልቆ ፍቅሩ ውስጥ ውስጤ ቢገባስ
አዝማች · Chorus
ባለኝ ይሄ መልካም ነገር
ቀደም ቢል ምን አለ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በከንቱ ያለፉት እነዚያ ቀኖቼ
ሳስበው ይቆጨኛል የዛሬን አይቼ
ዓለምን ሳይቀጫት ወይ እርሷ ሳትቀጨው
ብላቴና ሆኖ አንተን ላገኘ ሰው
ምንም እንደማያቅ ሞኝ ነው ቢሉትም
እንደእርሱስ ብልጥ የለም አላስተዋሉትም
ቁጥር 5 · Verse 5
እውነት ነው በጊዜ የበራለት
ቁጥር 6 · Verse 6
እርሱ እድለኛ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ