ከሁኔታ በላይ
Kehunieta Belay
2011 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ቁጥር 2 · Verse 2
ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ብዙ ጥያቄ እንቆቅልሽ እያለኝ
ግን እዘምራለሁ ሁሌ ደስተኛ ነኝ
ለእኔ የተከፈለው ትልቅ የደም ዋጋ
አይመጣጠንም ከሁኔታዬ ጋር
አዝማች · Chorus
እንቆቅልሼ እያለ
ችግር መከራ እያለ
ግን እዘምራለሁ ድል አለ
ግን እዘምራለሁ መልስ አለ (፪x)
ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ቁጥር 3 · Verse 3
በእንግድነት አገር ለጊዜው ምኖረው
በምታልፈው ዓለም ትቼው ለምሄደው
ቢሞላ ባይሞላ እኔ ምን ቸገረኝ
ስሄድ ምገባበት በሰማይ ቤት አለኝ
አዝማች · Chorus
እንቆቅልሼ እያለ
ችግር መከራ እያለ
ግን እዘምራለሁ ድል አለ
ግን እዘምራለሁ መልስ አለ (፪x)
ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ቁጥር 4 · Verse 4
እንዳላጉረመርም አፌን በምሥጋና
ሃዘንተኛ እንዳልመስል ፊቴ እያበራ
ኢሄ እንዴት ሆነ ለምትጠይቁኝ
ሁሉን የሚያስረሳ አባት ስላለኝ
አዝማች · Chorus
እንቆቅልሼ እያለ
ችግር መከራ እያለ
ግን እዘምራለሁ ድል አለ
ግን እዘምራለሁ መልስ አለ (፪x)
ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (፪x) (ጌታ የበላይ (፪x))
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ