አልከዳውም
Alkedawem
2011 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ
ይሄዳል አምላኩን ትቶ
ለሚያልፈው ለሚጠፋው
ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
ተራራ ሕይወት ዳገት ነው/መከራ ሕይወት ሰልፍ ነው
ለመኖር ሁሌ ትግል ነው
ቢሆንም ለተድላ ብዬ
አልሄድም አማላኬን ጥዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ
ይሄዳል አምላኩን ትቶ
ለሚያልፈው ለሚጠፋው
ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሌሊት ላይ ፀሐይ እንድትወጣ
ብፈልግ መች ይሆንና
ለሁሉም ስርአት አለው
እንስኪነጋ እጠብቃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ
ይሄዳል አምላኩን ትቶ
ለሚያልፈው ለሚጠፋው
ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ለእኔ ያስቀመጠውን
ለማንም እንደማይሰጠው
ገብቶናል ተረድቻለሁ
እርሱን ትቼ የት እሄዳለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ
ይሄዳል አምላኩን ትቶ
ለሚያልፈው ለሚጠፋው
ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
አልከዳውም ይሄን ሳወራ
ሞራልም አይደል ፉከራ
ከልቤ እወደዋለው
ያለ እርሱ እንዴት እኖራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ
ይሄዳል አምላኩን ትቶ
ለሚያልፈው ለሚጠፋው
ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ