የነፍስ አባቴ
Yenefs Abatie
2011 · ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ዋስ ጠበቃዬ (፪x) ካህኔ
ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የእርግብ የፍየል ደም ይፍሰስ
መሰዊያ ላድርጋቸው እንድዱት
የህዝቡ ኀጢአት እንዲሰረይለት
ሚቃጠል መስዋዕት ይቅረብለት
ይህ ስርአት ቀረ (፬x)
መስዋዕቴ ኢየሱስ ሆነ
መስዋዕቴ የከበረ (፪x)
አዝማች · Chorus
ዋስ ጠበቃዬ (፪x) ካህኔ
ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኀጢአትን ማስወገድ የማይችሉ
መስዋዕት ሁልጊዜ ሲያቅርቡ
እርሱ ግን ለአንዴ ፈጽሞ
ቀደሰኝ እራሱን አቅርቦ
የአዲስ ኪዳን ልጅ ነኝ (፬x)
የተሻለ ካህን አለኝ
የተሻለ ኪዳን አለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ዋስ ጠበቃዬ (፪x) ካህኔ
ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቃልኪዳን ከእኔ ጋር አደረገ
ህጉንም በልቤ አስቀመጠ
በአዲስና በሕያው መንገድ
አስገባኝ በስጋው በደም
የአዲስ ኪዳን ልጅ ነኝ (፬x)
የተሻለ ካህን አለኝ
የተሻለ ኪዳን አለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ዋስ ጠበቃዬ (፪x) ካህኔ
ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር የራሱን ፍቅር የገለጠበት
ስጦታው እንዴት ካለ ሞት እኔን ያዳነበት
ተአምር የምለው በሕይወቴ
ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ
ኦ ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ (፪x)
የውስጤን ሁሉ ማሳየው ሚስጥረኛዬ
በአብ ቀኝ የሚቆምልኝ ጠበቃዬ
ሚረዳኝ ደግሞም ሚረዳኝ ሊቀ ካህኔ
ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ
ኦ ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ