Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እዩልኛ

Eyulegna

2011 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምን ነካት ምን ነካት ምን ሆነች አትበሉ

ባይሆን የነካኝን ኢየሱሴን እዩ

እዩልኛ እንዲህ ያዘመረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ

እዩልኛ አንዲህ ያስጨፈረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

ነፍሴን ለታደጋት ባለውለታዬ

አውልቆ ለጣለው እድፋሙን ልብሴን

ብንከባለልለት በሰበብ ባስባቡ

ምን ነካት ያላቹህ እኔን አትታዘቡ

ገና ገና አመልካለሁ ፣ ገና ገና እዘምራለሁ

ገና ገና እሰግዳለሁ ፣ ገና ገና እዘላለሁ

ምን ነካት ምን ነካት ምን ሆነች አትበሉ

ባይሆን የነካኝን ኢየሱሴን እዩ

እዩልኛ እንዲህ ያዘመረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ

እዩልኛ አንዲህ ያስጨፈረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

ስላልጠገበች ነው የዓለም ነገር

እግዚአብሔር ቤት መጥታ እንዲህ ምትጨፍር

አትበሉ የልጅ ነገር በቃ ቆርጦልኛል

አሁን የሚያዘልልለኝ ሌላ እውነት ገብቶኛል

ገና ገና አመልካለሁ ፣ ገና ገና እዘምራለሁ

ገና ገና እሰግዳለሁ ፣ ገና ገና እዘላለሁ

ምን ነካት ምን ነካት ምን ሆነች አትበሉ

ባይሆን የነካኝን ኢየሱሴን እዩ

እዩልኛ እንዲህ ያዘመረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ

እዩልኛ አንዲህ ያስጨፈረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

በዉበት በመንፈስ ከሆነ ከውስጤ

እረፊ አትበሉኝ ላምልክ እንደልቤ

ከዚም በላይ ካለ ምናለ ባደርገው

የተሰራልኝን እኔ ነኝ የማውቀው

ገና ገና አመልካለሁ ፣ ገና ገና እዘምራለሁ

ገና ገና እሰግዳለሁ ፣ ገና ገና እዘላለሁ

ምን ነካት ምን ነካት ምን ሆነች አትበሉ

ባይሆን የነካኝን ኢየሱሴን እዩ

እዩልኛ እንዲህ ያዘመረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ

እዩልኛ አንዲህ ያስጨፈረኝ እኔን የኢየሱሴን ስራ

እዩልኛ አደናንቁልኛ ፣ እዩልኛ

በአይምሮዬ ብሆን እኔስ ለሰው???

????? ለአምላኬ ትልቅ ለሆነው

አቀርብለታለሁ መስዋዕቴን በሙሉ

መቼም ዝም አልልም ምድር ፍጥረት ስሙ

ገና ገና አመልካለሁ ፣ ገና ገና እዘምራለሁ

ገና ገና እሰግዳለሁ ፣ ገና ገና እዘላለሁ

ገና እዘላለሁ ገና ፣ ገና እሰግዳለሁ ገና

ኢየሱሴ ለታደገኝ ለጌታዬ ፣ ገና እዘላለሁ ገና

ገና ገና (፬x) ገና ገና (፬x) (ገና እሰግዳለሁ ገና)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ