ንቃ
Neqa
2011 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያልተማረውን ተመራማሪ
የዚ ቤት ጌታ ነው ባለዲግሪ
ያሞካሹታል በዘፈናቸው
ያቺኑ ሳንቲም እንዲሰጣቸው
(ኦ) ሆያ ሆያ ሆዬ ሆ (፪x)
ይህ ሆያ ሆዬ መልኩን ቀይሮ
ትንቢት በሚለው ስም ተሸፍኖ
እውነት በሚመስል ፍፁም ድራማ
ተቀነባብሮ እኛም ቤት ገባ
አዝማች · Chorus
ንቃ ክርስቲያን ንቃ
በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው እንደልቡ ዝሙትን ሰርቶ
በእርኩሰትና በአመጽ ተሞልቶ
ብለው ይሉታን አንተ ጐበዝ
እግዚአብሔር መጣ ሊባርክህ
(ኦ) ሆያ ሆያ ሆዬ ሆ (፪x)
ሰርቆ አጭበርብሮ የሚያመጣውን
መልካም ነው ብሎ ቢሰጥ ገንዘቡን
የበለጠውን ደግሞ እንዲያመጣ
አበዛዋለሁ ይልሃል ጌታ
(ኦ) ሆያ ሆያ ሆዬ ሆ (፪x)
ትክክለኛ ነቢዮች አሉ
የጌታን ብቻ የሚናገሩ
እነርሱንማ መች ሊሰሟቸው
ደፍሮ ይሏቸዋል ሟርተኛች ናቸው
አዝማች · Chorus
ንቃ ክርስቲያን ንቃ
በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መንፈስ ቅዱስን ቃሉ እንደሚለው
ሌባውን ሌባ ጨዋ አይለው
አንተ ያልሆንከውን ነህ የሚልህ
ሊጠቅም አይደለም ነው ሊገድልህ
አዝማች · Chorus
ንቃ ክርስቲያን ንቃ
በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ትክክለኛ ነቢዮች አሉ
የጌታን ብቻ የሚናገሩ
እነርሱንማ መች ሊሰሟቸው
ደፍሮ ይሏቸዋል ሟርተኛች ናቸው
አዝማች · Chorus
ንቃ ክርስቲያን ንቃ
በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ