ከወደድኩህ
Kewededkuh
2011 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ፍቅር ጌታ ጌታ
ፍቅር ኢየሱስ አንተ ብቻ
አንተ ብቻ"
አዝማች · Chorus
ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ
ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 2 · Verse 2
የአንተ ፍቅር እንከን የሌለበት
አሳልፎ ነፍስን እስከ መስጠት
ከዚህ ዕውቀት መማር እንኳን ባልችል
እኔ አፍቅሬ አይቻለሁ በምድር
አዝማች · Chorus
ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ
ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰው ስጥተኀኝ ወድጄ ከልቤ
ስገልጥለት ፍቅሬን በስራዬ
ሚከፈለውን ዋጋ ከፍያለሁ
በሕይወቴ ብዙ አሳልፊያለሁ
አዝማች · Chorus
ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ
ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ፍቅር ማለት እራስን መስጠት ነው
ለወደዱት ታማኝ መሆን
ለአንተ ያለኝን ፍቅር ስፈትሸው
ወድሃለሁ ምለው ውሸቴን ነው
አዝማች · Chorus
ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ
ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ምላሽ መስጠት ለአንተ ለፍቅርህ ሚሆን
ከወደድከኝ ጌታ ላቅርብልህ ምላሽ
አንደበቴ በጣም እንደምወድህ
ቢመሰክር ውዴ ማሬ ብልህ
ምን ይጠቅማል ቃላት ብደረድር
ተግባር የለሽ ከሆነ የኔ ፍቅር
አዝማች · Chorus
ከኖርኩልህ የእውነቴን የእውነቴን ልኑርልህ
ከመሰልኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልምሰልህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 6 · Verse 6
ከአፌ የሚወጣው ክሽን ያለ ያማረ
ስራዬ የዓለም ድኖ እንዳልዳነ
የእውነት ብወድህ ይሄ ይለውጠኛል
ቃሌን ከተግባሬ አንድ አድርግልኝ
አዝማች · Chorus
ከኖርኩልህ የእውነቴን የእውነቴን ልኑርልህ
ከመሰልኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልምሰልህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 7 · Verse 7
አንተ ትቀጣለህ ሃይለኛ ነህ ብዬ
እሳት እንዳልጣል ሲኦልን ፈርቼ
ይህን አልፈልግም ባፈቅርህ በቂ ነው
ላፈቀሩት መኖር አይከብድም ቀላል ነው
አዝማች · Chorus
ከኖርኩልህ የእውነቴን የእውነቴን ልኑርልህ
ከመሰልኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልምሰልህ
ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ
ቁጥር 8 · Verse 8
የምትወደኝ ጌታ በዘለዓለም ፍቅርህ
አንዴ ወደኀኛል በዘለዓለም ፍቅርህ
ኢየሱስ ብቻ የልቤ ወዳጅ ነህ
የነፍሴ ወዳጅ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ