Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተይ ነፍሴ

Tey Nefsie

2011 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ

ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (፪x)

እርስት አለ ተነሽ እሩጪ ፣ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ

ክብር አለ ተነሽ እሩጪ ፣ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ

ነፍሴ ሆይ እባክሽን ስሚ ፣ ልምከርሽ በደምብ አስተውዪ

እያቸው በምድር የሚሮጡ ፣ ለሚጠፋው አክሊል ሲተጉ

እርግጥ ነው ክርስትና ያማል ፣ ከኖሩ ዋጋ ያስከፍላል

ከታገልሽ ሁሉም ነገር ያልፋል ፣ ጠብቂ ኢየሱስ ይመጣል

ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ

ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (፪x)

እርስት አለ ተነሽ እሩጪ ፣ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ

ክብር አለ ተነሽ እሩጪ ፣ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ

እረኛ እንደሌለሽ አትሁኚ ፣ እንደማንም መንገድ ላይ አትቅሪ

ስጋሽን ጉሽም አድርገሽ ይዘሽ ፣ ወደ ርስትሽ ግቢ ጨክነሽ

ችግሩን መከራውን መቅመስ ፣ ግድ ነው ብድረ በዳን ማለፍ

በሜዳው በትዕግስት እሩጪ ፣ አቃተኝ ብለሽ አታቋርጬ

ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ

ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (፪x)

እርስት አለ ተነሽ እሩጪ ፣ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ

ክብር አለ ተነሽ እሩጪ ፣ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ

ዮሴፍን ወንድሞቹ የጠሉት ፣ ለአውሬ ጉድጓድ ውስጥ የጣሉት

ያ ሁሉ ግፍ የደረሰበት ፣ የእግዚአብሔር ሃሳብ ስላለበት

እንዲህ ያለው ምስክር እያለሽ ፣ ተይ ነፍሴ ለምን ትደክሚያለሽ

ፈተና ለጊዜው ያሳዝናል ፣ ኋላ ላይ መልካም ፍሬ ያፈራል

ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ

ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (፪x)

እርስት አለ ተነሽ እሩጪ ፣ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ

ክብር አለ ተነሽ እሩጪ ፣ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ

እግዚአብሔር የሰጠሽን ተስፋ ፣ ሚያስጥሉ ብዙ ናቸውና

አንቺ ግን ታላቅ ዋጋ እንዳለሽ ፣ አትዘንጊ ምድራዊውን አይተሽ

የእምነትሽን ጀማሪ ፈጻሜ ፣ ምሳሌሽን ኢየሱስን እዬ

ጨርሰሽ የጀመርሺውን ፣ ተቀበይ ሽልማትሽን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ