እመለሳለሁ
Emelesalehu
2011 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ብዙዎች እንደፈለጋቸው
አንተንም ሳይፈሩ የሚኖሩ ናቸው
ቁጥር 1 · Verse 1
ሲላቸው እንደምኞታቸው ቃልህን ይገልጻሉ
እራሳቸው ስተው ሌላውን ያስታሉ
አሉ ደግሞ ጥቂት አንተን የሚፈሩ
ምህረትህን ታምነው በጽድቅ የሚኖሩ
ታጋሽ ቸር ሩህሩህ ምህረትህ የበዛ
ለእነሱ ደግ ነህ ጨካኝ ከተቆጣ
እኔ ከእነዚህ ጋር ፈጥኜ እስማማለሁ
ላለፈው በደሌ ንስሃ እገባለሁ
ድንገት ሳትጥለኝ ዛሬ እመለሳለሁ
እመለሳለሁ ፍሬም ማያፈራ የደረቀ እንጨት
ማይጠቅም ዛፍ ተቆርጦ መጣል ነው በማይጠፋው እሳት
ልትመጣ ነው ክብርህን ልትገልጥ ቤትህን ልታጠራ
ኀጢአት ልትቀጥፍ ጅራፍህን ይዘህ ተነስተሃልና
አይሆንም ብሎ ማነው ባለስልጣን የሚከለክልህ
እንዴ ከያዝከኝ የትኛው ብርቱ ነው ከእጅህ የሚያስጥለኝ
እመለሳለሁ የኔ መጨረሻ የኔ እድል ፈንታዬ
እመለሳለሁ እንደ እንጨቱ እንዳይሆን መልሰኝ ጌታዬ
መልሰኝ ጌታዬ መልሰኝ
አዝማች · Chorus
ብዙዎች እንደፈለጋቸው
አንተንም ሳይፈሩ የሚኖሩ ናቸው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሲላቸው እንደምኞታቸው ቃልህን ይገልጻሉ/ይጠቅሳሉ
እራሳቸው ስተው ሌላውን ያስታሉ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ