ጉልበት ሆንከን
Gulbet Honken
ትራክ 6 · 4:25 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የመንፈሱ ኃይል እረድቶናል
መሸሸጊያ ዋሻ ሆኖልኛል
ጠላታችንን አዋርዷል
ከክበር ወደ ክብር አሻግሮናል
አዝማች · Chorus
እናመስግንሃለን ጉልበት ሆንከን
እናከብርሃለን ብርታት ሆንከን
ጌታ/ኢየሱስ ተመስገን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጨለማችን ይኸው በአንተ በራ
እስራታችንም ተፈታ
ክበር ለዘለዓለም ክበር
ወደር አቻ የለህም
አዝማች · Chorus
እናመስግንሃለን ጉልበት ሆንከን
እናከብርሃለን ብርታት ሆንከን
ጌታ/ኢየሱስ ተመስገን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በመከራችን ረድኤት ሆንከን
በክንድህም ብርታት እዚህ አደረስከን
ለክብርህም ቆመን እንዘምራለን
ታላቅነትህን እናውጃለን
አገነነው ለእኔስ ምህረቱን (፬x)
በዝቶልኛል ለእኔስ ቸርነቱ (፬x)
ያኔ ምን እመስል ነበር
በኃጢአት ገመድ ታስሬ
ኢየሱስ ስትመጣ ግን ወደ እኔ
ከላዬ ወደቀ ቀንበሬ (፪x)
ምን ልበል ዛሬ (፪x)
ክበር (፫x) ኢየሱስ ውዴ
ንገሥ (፫x) ኢየሱስ ውዴ
አገነነው ለእኔስ ምህረቱን (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ