Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሥመ ገናና

Seme Genana

ትራክ 9 · 4:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በአዲስ ቅኔ ዜማ ደግሞ በዝማሬ

ክብርን እሰጣለሁ ጌታ ለአንተ ዛሬ

ሰማይ ሰማያትም ክብርን ለአንተ ይስጡ

ምድርም ዕልል ትበል ክብር ይሁን ለእርሱ

ምሥጋናውን አምጡ ለእርሱ ለንጉሡ

ለንጉሡ ምሥጋና እናቅርብ እንደገና (፪x)

ኃይል የእግዚአብሔር ነው ሁሉን የሚገዛ

እርሱን እናድንቀው ይክበር በምሥጋና

በዘመናት ውስጥ ሁሉን የቻለ

ጌትን የሚተካ ኧረ ማን አለ

በክብር ላይ ክብር ክብርን ደርበህ

ደግሞም በሰማያት ከፍ ብለህ

በሚያስፈራ ግርማ ብርሃንን ለብሰህ

አንተ ትኖራለህ ለዘለዓለም

ጌታ ትኖራለህ ለዘለዓለም

ኢየሱስ ትኖራለህ ለዘለዓለም

ከአባቶቻችን ጋር ቀድሞ የነበረው

የነአብርሃም አምላክ ዛሬም ጉልበታም ነው

ክንዱ አይዝል አይደክም ከቶ አይታክተው

እርሱ ኧረ እርሱ ነው ማነው የሚችለው

ከአምልክቶች ሁሉ ክንዱ የበረታ ነው

ብርቱ ነው የበረታ አክብሩት በዕልልታ (፪x)

አማኑኤል (፫x) ከፍ ከፍ በል

ኤሎሂ (፫x) የሚመስልህ የለም

እግዚአብሔር (፫x) ለዘለዓለም ክበር (፪x)

ውዴ አቤት ግርማህ አስፈሪ ነው

ኢየሱስ የክብርህ ፀዳል ያበራል

ውበትህ ከሰው ልጆች ያማረ

ሥምህ ታላቅ ኃይል አለው ገናና ነው

ሥመ ገናና ነህ ገናና

ሥመ ገናና

ገናና ታላቅ ነህና (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ