Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ብርሃን ወጣልኝ

Berhan Wetalegn

ትራክ 1 · 6:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከፍ በል በማደሪያ ላይ እግዚአብሔር

በዙፋንህ ላይ እግዚአብሔር

በመቅደስህ ውስጥ እግዚአብሔር (፪x)

ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርክልህ (፪x)

በሰማይ በምድር አንተ ጌታ ነህ (፪x)

ምላስም በፍጥረት ታላቅ ነህ ይበልህ

ፅድቅህን ያውራልህ

ልዑል ማደሪያህን ይሙላ (፬x)

ማደሪያህን ይሙላ

ምሥጋናዬ አንተን ያክብርህ ጌታዬ

ክብርህን ይሙላው ዕልልታዬ (፪x) ሃሌሉያ

ክብር ለሆነው ገናና

እሰዋለሁኝ ምሥጋና (፪x) ሃሌሉያ

ምሥጋና (፪x) ለጌታ እንደገና

ዝማሬ (፪x) ለኢየሱስ ይሁን ዛሬ (፪x)

ያደረገልኝ እጅግ ብዙ ነው

በዕልልታዬ መቅደሱን ልሙላው (፪x)

ውለታው ያለባችሁ አመስግኑት

ቅዱስ ቅዱስ ብላችሁ ስገዱለት

ፍቅሩም የበዛላችሁ አሸብሽቡ

በምሥጋናም ማደሪያው ግቡ (፪x)

ምሥጋና (፪x) እላለሁ

ዝማሬ (፪x) እላለሁ

ዕልልታ ዕልልም እላለሁ

እኔ ከሞት ድኛለሁ (፪x)

መድኃኒቴ ለእኔስ እጅጉን ልዩ ነህ (፪x)

ከሲዖልም መሃል አንተ ታወጣለህ (፪x)

እግዚአብሔር አምላክ ሆነኝ ጨለማዬ በራ (፪x)

ብርሃን ወጣልኝ ስሆን ከእርሱ ጋራ

ስሆን ከእርሱ ጋራ (፪x)

ልዑል መጠጊያ ሆኖኛል (፬x)

እግዚአብሔር አምላክ ሆነኝ ጨለማዬ በራ (፪x)

ብርሃን ወጣልኝ ስሆን ከእርሱ ጋራ

ስሆን ከእርሱ ጋራ (፪x)

የነፍሴ ወዳጅ አንተ ነህ

በምክርህ ልቤን ታሳርፋለህ

በምክርህ ልቤን ታሳርፋለህ (፪x)

ሸለቆ ባይሞላ እኔ አላማርርም

በአምላኬ ላይ አፌን በከንቱ አልከፍትም

ከሁሉም ይበልጣል እንተን ማመስገን

ታላቅ ነህ እያሉ ክብርህን ማግነን

ታላቅ ነህ እያሉ ክብርህን ማግነን (፪x)

ክብርህ እንደ ደመና ሰማያትን ሸፍኗል

ኦሆ ሰማያትን ሸፍኗል

ምሥጋና ለዘለዓለም ለሥምህ ይገባሃል

ኦሆ ይገባሃል ኦሆ (፫x)

ክብርህ እንደ ደመና ሰማያትን ሸፍኗል

ኦሆ ሰማያትን ሸፍኗል

ምሥጋና ለዘለዓለም ለሥምህ ይገባሃል

ኦሆ ይገባሃል ኦሆ (፯x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ