Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የለህም እኩያ

Yelehem Ekuya

ትራክ 12 · 5:22 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ክቡር (፫x) ነህ ክቡር ነህ

ኃያል (፫x) ነህ ኃያል ነህ

ቅዱስ (፫x) ነህ ቅዱስ ነህ

አባት አንተን ላምልክህ (፪x)

ላምልክህ ኦ ላምልክህ (፪x)

አምላክ ነህና የዘለዓለም አንተ (፪x)

ንጉሥ ነህን የዘለዓለም አንተ (፪x)

ዝቅ ብለን እንሰግድልሃለን

ደስ እያለን እናመልክሃለን

አምላክ ነህና የዘለዓለም አንተ (፪x)

ንጉሥ ነህና የዘለዓለም አንተ (፪x)

ሰባቱን ማኅተም በእጆቹ የያዘ የፍጥረታት ጌታ

እንተ ግን ችለሃል ሁሉን ልትረታ

ማህተሙን ልትፈታ

ኪሩቤል ሱራፌል ያመሰግኑሃል ያሞጋግሱሃል

ከእግሮችህ ሥር ሆነው ቅዱስ ነህ ይሉሃል

ክብርን ይሰጡሃል

አንተ ብቻ ጌታ

አንተ ብቻ ንጉሥ

ነህና ኢየሱስ (፪x)

አምላክ ነህና የዘለዓለም አንተ (፪x)

ንጉሥ ነህን የዘለዓለም አንተ (፪x)

ዝቅ ብለን እንሰግድልሃለን

ደስ እያለን እናመልክሃለን

አምላክ ነህና የዘለዓለም አንተ (፪x)

ንጉሥ ነህና የዘለዓለም አንተ (፪x)

በምሥጋና የተፈራ በቅድስና የከበርክ

በሞገስ ላይ ሞገስ ለብሰህ

በኪሩቤል ላይ የተቀመጥክ

ሰማይና ምድር የአንተን ክብር አወሩ

ፍጥረታትም ደስ አላቸው ለሥምህ ዘመሩ (፪x)

ኦ ሃሌሉያ (፬x)

ጌታ ኢየሱስ የለህ እኩያ

ኦ ሃሌሉያ (፪x)

ከፍ ባለ ረጅም ዙፍን ላይ

እጅግ ባማረ መንበር ላይ

ተቀምጦ ያለ በሰማይ

እርሱ ነው እግዚአብሔር ኤልሻዳይ (፪x)

ኤልሻዳዩ እግዚአብሔር) (፪x) ዛሬም ክበር

ኤልሻዳይ ጌታ ኢየሱስ (፪x) ዛሬም ንገሥ

እንተ ለዘላለም ሕያው ነህ (፪x) በክብር ያለህ

እንተ ለዘላለም ሕያው ነህ (፪x) በክብር ያለህ

የአብርሃም የይስሃቅ የያዕቆብ አምላክ

ዛሬም ተመለክ ዛሬም ተወደስ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ