አልቆጥብም ድምጼን
Alqotebem Demtsien
ትራክ 10 · 4:01 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዕልል እላለሁ በመቅደሱ
ክብርን እሰጣለሁ ለንጉሡ
ዝቅም እላለሁ በዙፋኑ
አልቆጥብም ድምጼን ሁሌ እዘምራለሁ
ክብር ለሚገባው ክብርን እሰጣለሁ
አልቆጥብም ድምጼን ሁሌ እዘምራለሁ
ክብር ለሚገባው ክብርን እሰጣለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋናዬ በፊቱ ይብዛና
አምልኮዬ በፊቱ ይብዛና
ሽብሸባዬ በፊቱ ይብዛና
ይክበርልኝ ኢየሱስ እንደገና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉም በእግዚአብሔር ኃይል እጅግ ቀላል ነው
ተራራውን ሜዳ ማድረግ አይሳነው
በምሥጋና ሁሉ ላይ ምሥጋናን ጨምሮ
በቤቱ ያኖረኛል ይኸው አሳምሮ
በቤቱ ያኖረኛል ይኸው አሳምሮ (፪x)
አዝማች · Chorus
የኃያላንን ቀስት ተሰብራለህ
ለደካማው ኃይልን ታስታጥቃለህ
ምስኪኑን ከመሬት ታነሳለህ
ባማረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣዋለህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ይህ ሆኗል በሕይወቴ
ይድረስ ለእርሱ መስዕዋቴ (፪x)
አትታበዩ በኩራት አትናገሩ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይህንን አውሩ
የሞትን አውጅ እርሱ ይሽራል
ባማረ ፈረስ ላይ ያስቀምጣል
ባማረ ፈረስ ላይ ያስቀምጣል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ