Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምሥጋና ይወዳል

Mesgana Yewedal

ትራክ 7 · 6:16 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምሥጋና ለጌታ ይድረስ እንደገና

ዝማሬ ለኢየሱስ ይሁን እንደጋና

በዙፋኑ ላለው ይድረሰው ምሥጋና

ለጌታ ለኢየሱስ ይሁን እንደገና (፪x)

ምሥጋናን ይወዳል እርሱ

አምልኮን ይወዳል እርሱ

ዝማሬን ይወዳል እርሱ

ዕልልታን ይወዳል እርሱ

ክብርን እንስጠው ለንጉሡ (፪x)

ምሥጋና ዝማሬ አምልኮ

ስግደትም ለአንተ ነው ጌታ

ስግደትም ለአንተ ነው

ስግደትም ለአንተ ነው (፪x)

ይገባሃል ጌታ ይገባሃል ውዴ

ይገባሃለ ኢየሱስ ስለሆንክ ንጉሤ (፪x)

በበጉ ዙፋንን ፊት ሆነን በደስታ (፪x)

ክብርን እንሰጣለን ይክበርልን ጌታ (፪x)

ከማደሪያው ይድረስ ይግባ ምሥጋናችን (፪x)

ዕልልታ ያውደው ይድመቅ አምላካችን

ይድመቅ አምላካችን (፪x)

እስቲ ዕልል ዕልል በሉለት (፪x)

እናሸብሽብ እንስገድለት

እናሸብሽብ እንስገድለት (፪x)

ማንም በማይቀርበው ብርሃን ተከበሃል

ጌታዬ ኢየሱስ አንተን ማን ይቀርብሃል (፪x)

ፊትህ እንደ ፀሐይ ፀዳል ያበራል

ጨለማ መቼ ፊትህ ይቆማል

ጨለማ መቼ ፊትህ ይቆማል (፪x)

አቻም የሌለህ አምላክ ነህ

እኔ እሰግዳለሁ ለክብርህ

በአዲስ ቅኔ እቀኛለሁ

ለአምላኬ ለአንተ አሸበሽባለሁ

እሰግዳለሁ ለአምላኬ ለንጉሡ

ክብር ይሁንለት በመቅደሱ

እቀኛለሁ ለኢየሱስ ለንጉሡ

ክብር ይሁንለት በመቅደሱ (፪x)

ኦሆ ክብር ይድረስህ (፫x)

ኢየሱስ ዛሬም ጌታ ነህ (፪x)

እስቲ ዕልል ዕልል በሉለት (፪x)

እናሸብሽብ እንስገድለት

እናሸብሽብ እንስገድለት (፪x)

ኦሆ ክብር ይድረስህ (፫x)

ኢየሱስ ዛሬም ጌታ ነህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ