ነፍሴ ሆይ
Nefsie Hoy
ትራክ 4 · 5:37 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
አጥንቶቼም የተቀደሰ ሥሙን
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ
ምሥጋናውንም አትርሺ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ያለሽ
በደልሽንም ሁሉ ያላሰበ
ሕይወትሽን ከክፍት ያዳነ
በምህረቱ በቸርነቱ የከለለ
ማነው (፬x)
ኢየሱስ እኮ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
አጥንቶቼም የተቀደሰ ሥሙን
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ
ምሥጋናውንም አትርሺ
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴ ያዳነሽ ውቡ አበባ
ኢየሱስ ነው የሳሮን ጽጌረዳ
በደም ተጨማልቀሽ ከሩቅ ያየሽ
በመስቀል ላይ ሆኖ የወደደሽ
እርሱ ነው የሳሮን አበባ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
አጥንቶቼም የተቀደሰ ሥሙን
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ
ምሥጋናውንም አትርሺ
ቁጥር 3 · Verse 3
ብርሃንም ሆኖ ብርሃንን አሳየሽ
ጨለማሽን ገፎ ሕይወትን አደለሽ
እግዚአብሔር በክብር በኢየሱሱ ሰወረሽ
የመንግሥቱ ዜጋ ዜጋዊ አረገሽ
ነፍሴ ምን ትያለሽ ኧረ ይህን ጌታ (፬x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ
አጥንቶቼም የተቀደሰ ሥሙን
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ
ምሥጋናውንም አትርሺ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ