Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የመማፀኛ ከተማዬ

Yemematsegna Ketemayie

ትራክ 3 · 4:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኃጢአትን ሰርቼ ሊገድሉኝ ሲያሳድዱኝ

በመማፀኛ ከተማ ውስጥ ዘልዬ ገባሁኝ

የመማፀኛ ከተማዬ ጌታ ኢየሱሴ

በእርሱ ተሸሽጋ አረፈች ነፍሴ (፪x)

ሰለሞን የሰራው መቅደስ ፈረሰ

የኢያሪኮም ግንብ በጩኸት ወደቀ

የእኔ ግን መሸሸጊያዬ ተናውጦም አያውቅም

አይወድቅም ኢየሱስ አይነቃነቅም

ኃጢአትን ሰርቼ ሊገድሉኝ ሲያሳድዱኝ

በመማፀኛ ከተማ ውስጥ ዘልዬ ገባሁኝ

የመማፀኛ ከተማዬ ጌታ ኢየሱሴ

በእርሱ ተሸሽጋ አረፈች ነፍሴ

የሙሴ መሸሸጊያ ምድረ በዳ ነው

የእኔ ግን ማምለጫ ሰማያዊ ነው

የያዕቆብ መሸሸጊያው የላባ ቤት ቀረ

የእኔ ግን ማምለጫ ኢየሱስ በሰማይ ከበረ

ኃጢአትን ሰርቼ ሊገድሉኝ ሲያሳድዱኝ

በመማፀኛ ከተማ ውስጥ ዘልዬ ገባሁኝ

የመማፀኛ ከተማዬ ጌታ ኢየሱሴ

በእርሱ ተሸሽጋ አረፈች ነፍሴ

መኖሪያዬ የእኔ የዘላለም አምላክ ነው

ጌታዬ ኢየሱስ የፀና ግንብ ነው

እግዚአብሔር መልካም ነው እኔ ምንም አልሆን

መሸሸጊያዬ ሆኗል በመከራ ቀን

ኃጢአትን ሰርቼ ሊገድሉኝ ሲያሳድዱኝ

በመማፀኛ ከተማ ውስጥ ዘልዬ ገባሁኝ

የመማፀኛ ከተማዬ ጌታ ኢየሱሴ

በእርሱ ተሸሽጋ አረፈች ነፍሴ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ