Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላኬ ይወደኛል

Amlakie Yewedegnal

ትራክ 2 · 4:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬ ይወደኛል እኔም እወደዋለሁ

ፍቅሩን ቸርነቱን በዘመኔ ቀምሻለሁ

በጊዜው አይቻለሁ አዲስ ነገር ሲሰራ

በሽተኛን ስትፈውስ ዓይነ ስውር ስታበራ (፪x)

ዎሆሆሆ

ለዘለዓለም ክብር

ለዘላለም ንገሥ (፪x)

እንባዬ ታብሶልኝ ከማደሪያው ገብቻለሁ

ሳልፈልገው ፈልጐ በእጆቹ ደርሻለሁ

ለወደደኝ ጌታ አምላኬ

እሰግዳለሁ ተንበርክሬ (፪x)

ዎሆሆሆ

ለዘለዓለም ክብር

ለዘላለም ንገሥ (፪x)

ጉልበትም ሆንህልኝ ጠላቴንም እረገጥኩት

ስለዚህም ወደድኩህ ክበር ክበርም አልኩህ

ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ

ለዘለዓለም ምትኖር ነግሥህ (፪x)

ዎሆሆሆ

ለዘለዓለም ክብር

ለዘላለም ንገሥ (፪x)

ተመሥገን እግዚአብሔር ኃይሌን አደስክልኝ

በኮረብታም አቆምከኝ ለዘለዓለም ክበርልኝ

ውዴ ፍቅርህ ማርኮኛል

ክበር ክበር ያሰኘኛል (፪x)

ድንቅ አድራጊ ባለሞገስ ባለዝና

እንዳልናወጥ እግሮቸን አፀና ምሥግና (፪x)

በፀጋው ዙፋን ሥር ምሥግና

በክብሩ ወንበር ፊት ምሥግና

እሰዋለሁ ለሆነው ገናና (፪x)

ድንቅ አድራጊ ባለሞገስ ባለዝና

እንዳልናወጥ እግሮቸን አፀና ምሥግና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ