እሰይ ኢየሱስ ክበር ክበር
Esey Eyesus Keber Keber
ትራክ 5 · 4:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤት (፬x) በታላቅ ሞገስ
እሰይ (፬x) ኢየሱስ ከበረ
ፍጥረታት ተገዙለት ኃያላን ሰገዱለት
ምሥጋና በማደሪያው ላይ
ከፍ አለ እጅግ በሰማይ
እርሱ ባለ ታላቅ ግርማ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የክብር ዘውድ: የጫነው
አቤት እርሱ ባለ ታላቅ ግርማ ነው (፪x)
የድል አክሊል የጫነው
በሰማያት በታላቅነት በደመናት ላይ የሚሄደው
በሞገስ ላይ ሞገስ ለብሶ ብርሃን የተጐናፀፈው
የተፈራ የተከበረ በውበቱ እጅግ ያማረ
ኢየሱስ ነው ለዘለዓለም በዙፋኑ ፀንቶ ያለ
እናመስግነው (፫x)
ኢየሱስ የለም መመስለው (፪x)
እንዳንተ ያለ ማነው (፪x)
እግዚአብሔር (፪x) ዘላለም የምትኖር
ኢየሱስ (፪x) ሥምህ የሚፈውስ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት (፬x) በታላቅ ሞገስ
እሰይ (፬x) ኢየሱስ ከበረ
ፍጥረታት ተገዙለት ኃያላን ሰገዱለት
ምሥጋና በማደሪያው ላይ
ከፍ አለ እጅግ በሰማይ
እርሱ ባለ ታላቅ ግርማ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የክብር ሰውን የቻለው
አቤት እርሱ ባለ ታላቅ ግርማ ነው (፪x)
የድል አክሊል የጫነው
በተቀደሰው ቅዱስ መቅደስ
በግርማ ሞገስ የሚመላለስ
እርሱ ነውና ጌታ ኢየሱሴ
ዘላለም ይክበር ይንገሥ በነፍሴ
ክቡር ነውና (፫x) እግዚአብሔር ሥመ ገናና
ንጉሥ ነውና (፫x) ኢየሱስ የጀግኖች ጀግና
አዝማች · Chorus
አቤት (፬x) በታላቅ ሞገስ
እሰይ (፬x) ኢየሱስ ከበረ
ፍጥረታት ተገዙለት ኃያላን ሰገዱለት
ምሥጋና በማደሪያው ላይ
ከፍ አለ እጅግ በሰማይ
እርሱ ባለ ታላቅ ግርማ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የክብር ሰውን የቻለው
አቤት እርሱ ባለ ታላቅ ግርማ ነው (፪x)
የድል አክሊል የጫነው
በሰማያት ሰማይ ያለ
ጥንትም በፊትም የነበረ
በዘመናት የሸመገለ
እግሩ እንደ ነሃስ የጋለ
ድምፁ ነጐድጓድ የሚያስፈራ
ብቻውን ድንቅ የሚሰራ
ደማቅ ብርሃን የተሞላ
እንደ ቀትር የሚያበራ
ኦ ኦሆሆሆ (፫x)
ብርሃን ይወጣል ከፊቱ
የክበር ፀዳል ነው ውበቱ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ