የኃያላን ኃያል
Yehayalan Hayal
ትራክ 11 · 5:43 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የኃያላን ኃያል የዘለዓለም ጌታ
መልካም መዓዛ ያለው የሕይወት ሽታ
እናከብረዋለን ነፍሳችን ነቅታ (፪x)
ውዳችን ከእልፍ የተመረጠ ነው
ክበር ክበር እንበለው
ንገሥ ንገሥ እንበለው
ቁጥር 1 · Verse 1
ውዳችን ከእልፍ የተመረጠ ነው
ክበር ክበር እንበለው
ንገሥ ንገሥ እንበለው (፪x)
በላይ በሰማይ ለከበረው
እንደ በግ ለእኔ የታረደው
የናሱን ደጆች ለሰባበረው
ምሥጋና ክብር ውዳሴ ይድረሰው
አዝማች · Chorus
የኃያላን ኃያል የዘለዓለም ጌታ
መልካም መዓዛ ያለው የሕይወት ሽታ
እናከብረዋለን ነፍሳችን ነቅታ (፪x)
ውዳችን ከእልፍ የተመረጠ ነው
ክበር ክበር እንበለው
ንገሥ ንገሥ እንበለው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቆጥሬ የማልዘልቀው ውለታ አለብኝ
ጌታ ኢየሱሴ ለእኔ የዋለልኝ
ምላሽ እንኳን ቢሆን በብዙ ጥቂት
ይኸው ምሥጋናዬ ወዳጄ ላለኸው በሰማይ
አዝማች · Chorus
የኃያላን ኃያል የዘለዓለም ጌታ
መልካም መዓዛ ያለው የሕይወት ሽታ
እናከብረዋለን ነፍሳችን ነቅታ (፪x)
ውዳችን ከእልፍ የተመረጠ ነው
ክበር ክበር እንበለው
ንገሥ ንገሥ እንበለው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ውበቱ የሚያምር ማነው እንደ ውዴ
ግርማው የሚያስፈራ ማን እንደ ንጉሤ
ነገሥታት ኃያላን አለቆች በሙሉ
ግሩም ነው ድንቅ ነው እያሉ ለሥሙ ይገዛሉ
አዝማች · Chorus
የኃያላን ኃያል የዘለዓለም ጌታ
መልካም መዓዛ ያለው የሕይወት ሽታ
እናከብረዋለን ነፍሳችን ነቅታ (፪x)
ውዳችን ከእልፍ የተመረጠ ነው
ክበር ክበር እንበለው
ንገሥ ንገሥ እንበለው
ቁጥር 4 · Verse 4
ውዳችን ከእልፍ የተመረጠ ነው
ክበር ክበር እንበለው
ንገሥ ንገሥ እንበለው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ