አባባ
Ababa
2010 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሲዖል ጣር ሲይዘኝ
የሞት ወጥመድ ሲከበኝ
ስማኝ ስለው አባባ
ጩኸቴ ጆሮው ገባ አባባ
አባቴ ቀንዴ ነው ረድኤቴ
አባባዬ አባባ ጩኸቴ ጆሮው ገባ አባባ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አለቴ አምባዬ (፪x)
ትምክህቴ ጦሬ ነው ጋሻዬ (፪x)
ሰማይ ዝቅ አለ አምላኬ ወረደ (፪x)
ከአፉ እሳት እየነደደ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቁጣው ወጣ ጌታዬ በራ
በቀል የእርሱ የአምላኬ የእርሱ ሥራ
ለሚጠላኝ ወደረኛ
ወየውለት ጌታ መጣልኛ
ለሚጠላኝ ወደረኛ
ወየውለት ዘመን መጣልኛ
በአንተ ቅጥሩን እዘላላሁ
በጭፍራው ላይ እሮጣለሁ
አጥፋ ብሎኝ አውጥቶአቸው
ቀስተ ሰይፉን አሳያቸው
በቀኝህ አስር ሺህ ወደቁ
ሳይቀርቡ ሺዎችም አለቁ
እንደጋሻ እውነቱ ከበበኝ
ከፍላፃ አስጣለኝ
አዝማች · Chorus
ሰማይ ዝቅ አለ አምላኬ ወረደ (፪x)
ከአፉ እሳት እየነደደ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃይልን ለበስኩ አስታጠቀኝ
የጠላቴን ጀርባ ሰጠኝ
እንደ ጭቃ ረገጥኳቸው
እንደ ትቢያ ፈጨኋቸው
መክበቡን ዙሪያዬን ከበቡኝ
አታልፍም ስንዝርም ብለውኝ
በስቃያቸው ላይ እየሳቅኩ
በሥምህ አሸነፍኩ
አዝማች · Chorus
ቁጣው ወጣ ጌታዬ በራ
በቀል የእርሱ የአምላኬ የእርሱ ሥራ
ለሚጠላኝ ወደረኛ
ወየውለት ጌታ መጣልኛ
ለሚጠላኝ ወደረኛ
ወየውለት ዘመን መጣልኛ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ