Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አስበኝ

Asebegn

2010 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬ ሆይ ቃሌን ስማ

ፀሎቴን አድምጥ ልመናዬ ይድረስልኝ

አንዴ አስበኝ ናልኝ አስበኝ

በአንተ ብቻ ተስፋ አለኝ

አንዴ (፪x) አስበኝ

ሌላ ጥያቄ መሻት የለኝ

ፀጋህ ሳያንሰኝ ምህረትሀ ሳይጎድል

ምነው መዛሌ ምነው መታለል

መንገድህ ባይሆን እንደመንገዴ

እድልን ስጠኝ አስበኝ አንዴ

አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (፪x)

አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (፪x)

አትሰብር ከቶ ቅጥቅጥ ሸምበቆ

መንፈሱ ደቆ ሰው ካንተ ርቆ

አታጠፋውም ሚጤሰውን ጧፍ

ግን ሳታስበኝ ጊዜው እንዳያልፍ

አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (፪x)

አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (፪x)

አሀአሀሀሀ አስበኝ

አሀአሀሀ አስበኝ

አስበኝ ጌታ አሀሀሀሀ

ከአለት ንቃቃት ተሸሽጌያለሁ

ክረምቱ ሲያልፍ ያኔ ወጣለሁ

ለምትል ነፍሴ ለተጨነቀች

የአንተን ጉብኝት አንዴ ትላለች

አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (፪x)

አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (፪x)

ያለቦታዬ ቦታን አግኝቼ

በምድያም ሀገር ሰውን ፈርቼ

ተነስ የሚል ድምፅ አንተ ፅኔ ሀያል

ስታስብ እንጂ ከየት ይሰማል

አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (፪x)

አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (፪x)

አስበኝ እንደቃልህ

አሀሀሀ የእኔ ጌታ እኔን አንዴ አስበኝ

አትሰብር ከቶ አስበኝ

መንፈሱ ደቆ እንደቃልህ

አታጠፋውም አምላኬ ሆይ

ግን ሳታስበኝ ጊዜው እንዳያልፍ

አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (፪x)

አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ