ጌታን ነው የያዝኩት
Gietan New Yeyazkut
2010 · ትራክ 11 · 6:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተ ባትደረስ ባታየኝ ኖሮ
አይዞህ ያለኝ ሰው ድንገት ተሰብሮ
ባበቃ ነበር እዛ ላይ እኔስ ታሪኬ
አዋጅ ባይሻር የሞቴ ባንተ ባምላኬ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሰው አለኝ አይደለም ያልኩት
ጌታን ነው እኔስ የያዝኩት (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መመኪያዬ መታመኛ ነው
እሱን ይዤ ታዲያ እንዴት ፈራለሁ (፪x)
ሰው አለኝ አይደለም ያልኩት
ጌታን ነው እኔስ የያዝኩት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በስብርባሪውም እደርሳለሁ እንጂ
አልቀርም ስምጬ ይዤ የአንተን እጅ
ይዤ ጌታን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ ሆ
ይሞታል እያሉ ይጠባበቃሉ
እሱን ይዞ ያፈረ ማንን ሰው ያውቃሉ
ይዤ ጌታን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ ሆ
አዝማች · Chorus
መመኪያዬ መታመኛ ነው
እሱን ይዤ ታዲያ እንዴት ፈራለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በእርግጥ ወጀብ ካለ ታንኳ አይለቀቅም
ና ካለኝ ግን ጌታ ልቀር አላስብም
ይዤ ጌታን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ ሆ
በድካም በብርታት አሳልፎ የማይሰጥ
እሱን መያዝ እንጂ ማዕበሉን ለማምለጥ
ይዤ ጌታን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ ሆ
አዝማች · Chorus
ሰው አለኝ አይደለም ያልኩት
ጌታን ነው እኔስ የያዝኩት (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ለዚህች አጭር ዘመን ለዚህች አጭር ጊዜ
ቅርት ይበል ሁሉም ዘላለሜን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ ሆ
አንዱም አላረካኝ አንዱም ውስጤ አልገባ
አንተን ስይዝህ ነው የደረቀው የኔ እንባ
ይዤ ጌታን ይዤ
ይዤ ጌታን ይዤ ሆ
አዝማች · Chorus
መመኪያዬ መታመኛ ነው
እሱን ይዤ ታዲያ እንዴት ፈራለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ