ይሰራል ጌታ
Yeseral Gieta
2010 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬማ አምላክ ነውና ዛሬም ይኖራል
ሳይለወጥ እየለወጠ ታሪክ ይሰራል
አምላኬማ አምላክ ነውና ዛሬም ይኖራል
ሳይቀየር እየቀየረ ታሪክ ይሰራል
ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ
አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ
ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል
ያለ ምሰሶ ሰማይ ቆሟል
ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ
አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ
ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል
ስንት ደካማ በዚያ ቆሟል
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ሥራህ
እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለ ጌታ የሚባል ብዙ ነገር ኖሮ
እንዴት ልቤ ይግባ ሀዘን እንጉርጉሮ
እንደሰው ልጅ ሀሳብ አይደለም መንገዱ
ለበጎ ነው እንጀ እሱን ለወደዱ
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ሥራህ
እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ
አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ
ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል
ያለ ምሰሶ ሰማይ ቆሟል
ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ
አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ
ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል
ስንት ደካማ በዚያ ቆሟል
በመጀመሪያ በፍጥረት ዓለም
ግዑዝም ሕያው ከአንተ ጋር የለም
ሁሉን ካመጣህ ከምንም ነገር
ዛሬም ስለ እኔ ተናግረህ አይቀር
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ሥራህ
እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ይሰራል ጌታ የአንተ ሥም
ወደ ላይ አይሄድም ደፍሮ ማንም
ይሰራል ጌታ የአንተ መንፈስ
ወደ እውነት ሁሉ መርቶ ሚመልስ
ይሰራል ጌታ የአንተ ሕግ
ፍትህ ያለበት ፍርድ የሚያደርግ
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ሥራህ
እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የተዋበና የተራቀቀ
የአምላኬ ሥራ እጅግ የላቀ
መፈጠር እንጂ መፍጠር ማን ችሏል
ማደስ ብቻ አይደል አዲስ ይሰራል
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ሥራህ
እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ