ቃልህ
Qaleh
2010 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አስጠጋኝ ወደ አንተ ወደ ጉያህ (፫x)
የልብህን እንዳውቅ እንድረዳ (፫x)
አስጠጋኝ ወዳጄ ወደ ስርህ (፫x)
ቃልህን በልቤ እንድሰውር እንዳኖር (፫x)
አዝማች · Chorus
መገኛ የእኔ ሥሬ ጎሳዬም ቢሆን ዘሬ (፪x)
ውበቴ ምለው ክብሬ ቃልህ ነው ቃሌና ግብሬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቃልህ አንተ ጌታ አንተም ቃልህ
አለማቱ ሁሉ የተገኙብህ
ቃልህ አንተ ጌታ አንተም ቃልህ
ሰማይና ምድሩ የተገኙብህ
አዝማች · Chorus
መገኛ የእኔ ሥሬ ጎሳዬም ቢሆን ዘሬ (፪x)
ውበቴ ምለው ክብሬ ቃልህ ነው ቃሌና ግብሬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላኬ በቃልህ ደስ ይለኛል (፫x)
ብዙ እንደማረከህ እንዳገኘህ ይሰማኛል (፫x)
ታመንኩኝ ተፅናናሁ ሳስበው (፫x)
ውስጤም ረሰረሰ ሳስገባው ስሆነው (፫x)
አዝማች · Chorus
መገኛ የእኔ ሥሬ ጎሳዬም ቢሆን ዘሬ (፪x)
ውበቴ ምለው ክብሬ ቃልህ ነው ቃሌና ግብሬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ቃልህ አንተ ጌታ አንተም ቃልህ
አለማቱ ሁሉ የተገኙብህ
ቃልህ አንተ ጌታ አንተም ቃልህ
ሰማይና ምድሩ የተገኙብህ
አዝማች · Chorus
መገኛ የእኔ ሥሬ ጎሳዬም ቢሆን ዘሬ (፪x)
ውበቴ ምለው ክብሬ ቃልህ ነው ቃሌና ግብሬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ